በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነስቷል
- ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
- “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
- ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃትሏል
(አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡