(አዲሱ ተስፋዬ/ READ IN PDF):- ከትላልቆቹ ያገራችን ባለስልጣናት ጀምሮ ታች እስካለው ሕዝብ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን
የበርካቶች መነጋገርያ ከሆነ ከራርሟል:: የሰሞኑን ግን ለየት የሚያደርገው ራሱን " ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” " በማለት የሚጠራው ድርጅት በማኅበሩና በተዋሕዶ
እምነታቸው ላይ ጽኑ አቋም ባላቸው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ላይ ለማንበብ የሚዘገንኑ (character assassinating) ጽሑፎችን እያስነበበ ነው ። ከዚህም አልፎ የ”ተሐድሶ” ቡድኖችንና አቡነ ጳውሎስን የተቃወሙ አባቶች ላይ ስማቸውን የሚያጠፋ በርካታ መጽሀፍት እስከመታተም ተደርሷል (አቡነ ሳሙአልን አቡነ አብርሃምን አቡነ ሚካኤል እና ሌሎች ጳጳሳትን ስም እያጠፉ የወጡት መጻህፍትን ያስታወሷል) አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸውና
የድረገጻቸውን
traffic rank ከመጨመር
የዘለለ አርቀው ማሰብ የተሳናቸው የፖለቲካ ዌብሳይቶችም እነዚህኑ ጽሑፎች
በየድረ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ለብዙዎች አስነብበዋል።
ጽሑፎቹን ያነበቡ በርካቶች የዋሀንም የችግሩን መሰረታዊ ምክንያት ባለመረዳት "የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳን ጦርነት"በማለት እንደዘበት ሲመለከቱትና ሲገረሙበት ይስተዋላል።
ውስጠ ሚስጥሩን ያወቁና ውዝግቡ "የውክልና ጦርነት " መሆኑን የተገነዘቡ ጥቂቶችም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ህልውናዋን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ” ችግር ውስጥ
መግባቷን ይተነትናሉ። ለመሆኑ ግን የማኅበረ ቅዱሳንና የ”ተሐድሶ” ገመና ምን
ይመስላል? ። ከሁለቱም በስተጀርባ ያለው አካል ማነው? የሁለቱ አካላት መሰረታዊ አለመግባባትስ ምክንያቱ ምንድነው?
ቅድመ ነገረ “ተሐድሶ”
በርካታ ሚሲዎናውያን ከረጅም ግዜ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ይታወቃል።
በተለይ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት
ሚሲዮናውያን ለዚህ
ተጠቃሾች ናቸው::
እነዚህ ሁለት
የሚሲዮን ቡድኖች እርስ በርስ የማይስማሙና የማይገናኙ ቢሆኑም የሚያመሳስላችው
ግን በርካታ ባህርያት ነበሯቸው ። ሁለቱም " ሀይማኖት ለመስበክ ነው የገባነው" ቢሉም ÷ በተግባር ግን በገቡበት
ሀገር ስራቸው ፖለቲካዊ ነበር ። የሁለቱም ሚሲዮናውያን ኢላማ ያልተጠመቀው ሕዝብ
ሳይሆን ባርባና በሰማንያ ቀኑ የተጠመቀው የተዋሕዶ ተከታከታይ እንደነበር በወቅቱ የተጻፉ የታሪክ ማስረጃዎች ያስገነዝባሉ። የካቶሊኮቹ ሚሲዮናውያን ይሄ ቅሰጣቸው ሲታወቅና ካገር
መባረራቸው እንደማይቀር ሲያውቁ እነሱን ወክሎ
የነሱን ስራ
የሚያስፈጽሙ " ቅባትና ጸጋ"
የሚባሉ ቡድኖችን ፈጥረው ፣ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ከሁለት ለመክፍልና አዳክሞ ለመጣል ከፍተኛ ስራ ቢሰሩም ያሰቡት ሳይሳካ ቤተ ክርስቲ ያንም
ሳትከፈል እስካሁን ቆይታለች።
“ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” ”
የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያንም የተጠቀሙት ተመሳሳይ ስልትና ሴራ ነው። በመጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ያስፈቀዱት "ሀይማኖት ለሌለውና ላረማዊው ወንጌልን ፣ ለሌላውም ክርስቲያን ደግሞ ስልጣኔን እናስተምራለን በማለት ሲሆን፤ ራእያቸውም “የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደግፋለን" የሚል ነበር ።ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በግዜው ለነበሩ የመንግስት አካላት ያስገቡት የተልእኮ እቅድ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ማገዝ እንጂ ሌላ ቤተ ክርስቲያን መክፈት ወይም ቤተ ክርስቲያኗን የሚቃወም ሥራ መስራት አልነበረም።
" In 1924 the Ethiopian missionary
Association was formed with a mission statement to revive the orthodox church
and not setup a separate church " [i]
ምንም እንኳን በወረቀት ያሰፈሩት ዓላማ ይሄ ቢሆንም በተግባር የሚያደርጉትና ያደርጉት እውነታ ግን
ከዚህ የተለየ ነበር ። ይህንንም የታሪክ ሊቃውንቱ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል
"Missionary efforts in Ethiopia have
generally had to goals: to reform the Ethiopian Orthodox Church and to
establish independent congregations taught and supervised by the missionaries.
The missionary effort of the nineteenth and twentieth centuries often ended up
doing both” [ii]
አሁን አሁን ራሳቸው የሚያውጧቸው ድርሳናት ላይ የወቅቱን የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን
የማደስ ( ሚሲዮናዊ ማድረግ)
ድብቅ
ዓላማቸውን እንዲህ ሲሉ
ገልጸውታል::
"Modernizing Ethiopian society
wasn’t the main agenda of protestant missionaries of the 17th century. Their
main agenda was reforming Ethiopian church".[iii]
ዋና ዓላማቸው በግልጽና በግልጽ እንዳስቀመጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ማደስ በሚል ፈሊጥ መከፋፈልና ማፈራረስ ነበር ።
ከራሳቸው ድርሳናት መረዳት
እንደሚቻለው ጻጋናቅባትን የካቶሊክ
ሚሲዮናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ለመከፋፈልና
አዳክሞ ለመገርሰስ የፈጠሯቸው
እንደሆኑ ሁሉ ፣
“ተሐድሶ” ም
( ኦርቶዶክስ ተሃድሶ) የፕሮቴስታንት
ሚሲዮናውያን ቤተ ክርስቲ ያንን ለመከፋፈልና
አዳክሞ ለመገርሰስ ይረዳቸው
ዘንድ የፈጠሩት
እንቅስቃሴ ነው ።
ኦርቶዶክስ
“ተሐድሶ” ፣ ሚሲዮናወያኑ
በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ
ከጥንት ጀምሮ አውጀው
የነበረውን ጦርነት በውክልና
የሚዋጋ (proxy war) ወኪል እንጂ
በራሱ የቆመ
ወይም ኢትዮጵያዊ
መሰረት ያለው ቡድን
አይደለም። የሚታዘዘውም ፣
የሚመራውም ፣
አይዞህ ባዮቹም እነዚሁ
ምስጢረ ብርቱዎቹ ሚሲዮናውያን
ናቸው። ነገር ግን
በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን
ጸሎትና ትጋት ያሰቡት
ለበርካታ ክፍለ ዘመናት
የተጠነሰሰ ሴራ ሳይሳካ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
እስክ 21ኛው
ክፍለ ዘመን
ደርሳለች። አሁን ባለንበት 21ኛው
ክፍለ ዘመንም
ካላፈው ስህተታቸው በመማር
አዲስ ወረራና
ደባ ጀምረዋል
። በመሰረቱ ማንኛውም
የሃይማኖት ድርጅት እምነቱን
ማሰራጨትና መብቱ ሊሆን
ይችላል ። በማያምኑበት
እምነት ቤት ውስጥ
ገብቶ ሌላውን መዝለፍ
፣ ለማፍረስ
ማሴር ግን ወንጀል
ነው ።
የደርግ መንግስት
ወድቆ አማጺው ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ የነበረውን ክፍተት በመጠቀም ከተለያዩ የሚሲዮን ድርጅቶች ቤተ ክርስቲ ያኒቷ ላይ የስድብና የትንኮሳ ውርጅብኝ ይዝንብ ጀመር። ከዛም አልፎ ተርፎ በወቅቱ ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴርና የአመራር
አካላት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዲሸሹና ቤተ ክርስቲ ያኒቷንም በተቻላቸው እንዲያዳክሙ የሚያሳስብ መልእክት ከነኝሁ ሚሲዮናውያን ቤተመንግስት ድረስ በድፍረት አስከመላክ ደረሱ ።መቀመጫውን አሜሪካን ያደረገው ዎርልድ ሚኒስትሪስ ለአቶ ታምራት ላይኔ የላከውና መላው ኣለም ያነበው ዘንድ በዌብ ሳይቱ እስካሁን የለጠፈው መልክት ቅንጫቢ ይሄንን ይመስላል::
To the Government of
Ethiopia:
My name is Jonathan
Hansen. I am an ordained minister of the Gospel of Jesus Christ, the living
God. I travel now primarily to countries where God has given me a message for
either a person, the Christian community, the government or the nation…
The divine warning from the Lord was:"Remove yourself from the
prostitute if you want to live!"
…
God in his mercy is telling the Ethiopian government to remove itself from the
influence of the Orthodox Church. It does not preach and teach the true Gospel
of Jesus Christ, but the doctrine of demons (fallen angels)….
"Your previous
government slept with the prostitute of death then; the current government is
also sleeping with this Angel of Death. Both governments listened and took her
advice. God has warned this present government to break away from her or it
will die too; that the next government will continue to sleep, eat and drink
with this same prostitute and together they will join others in going against
Israel. The prostitute is the Orthodox Church." [iv]
ወዲያውም ራሱን “ኦርቶ ጴንጤ” የሚል ቡድን ቤተ ክርስቲ ያንን ያምሳት ጀመር ። የዚሁ ቡድን ዓላማም አንድ ነበር- የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በማጥፋት በፕሮቴስታንታዊ አስተምሮ መተካት። ለዚህም ዓላማው መሳካት የመለመላቸውና በስውር ሲያሰለጥናቸው የነበሩት አንዳንድ የቀድሞው የሃይማኖተ አበው አባላት ቤተክርስቲያኒቱን አመሷት::በተለይ በሀረር ፣ ናዝሬት ባሉ አብያት
ክርስቲያናትና ምእመናን ላይ ከባድ ወከባና ውዥንብር ፈጠረ ። ጥቂት የማይባሉ ምእመናንም ከናት ቤተ ክርስቲ ያናቸው ለማስኮብለል ቻለ። ይሄው ራሱን ኦርቶ ጴንጤ እያለ የሚጠራው ቡድን ግን እንዳሰበው ብዙ
ርቀት ሳይጓዝ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከበርካታ የተዋሕዶ አባቶች ትጋት አናቱን ተመታ። በርካታ ፊታውራሪዎቹም ተወግዘው ተለዩ።
አዲሱ ስልት - ቤተ ክርስቲያኗ ጉያ ውስጥ ተደብቆ ኦርቶዶክስን መገዝገዝ
ይህንን የተመለከቱት አዝማቾቻችው ግን የተረፉት የ”ተሐድሶ” አባላት እስኪጠናከሩ
ድረስ አንገታቸውን ቀብረውና መስለው በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲቀመጡና ቤተ ክርስቲ ያኗን በስውር እንዲገዘግዙ መከሩ። ይህንንም
ምስጢር ፓስተሮቻቸው በተለያየ ግዜ ገልጸውታል::
“the movement grew
swiftly and incorporated evangelical themes into the orthodox liturgy.
Eventually it grew so large that the group was expelled from the orthodox
church. Now called the reform orthodox church , the 70,000 plus believers
maintain a connection to their orthodox roots but exibit an evangelical
emphasis .[v]
ይህም ራስን ደብቆ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ውስጥ ውስጡን መገዝገዙ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አዝማች የሆኑት አንዱ ፓስተር እንዲህ ሲሉ ገልጠውታል::
“They are doing a
good job of staying close enough to their roots to be attractive to other
orthodox believers and seekers”, one missionary said recently. [vi]
የዚህ ቡድን ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሚሲዮናውያን ካምፕ መለወጥ መሆኑ በመታወቁ ከቤተ ክርስቲያን ቢገለልም በርካታ አባላቱ ግን ራሳቸውን ደብቀው ውስጥ ውስጡን ሲደራጁ የቤተ ክርስቲያን ያልሆነ ትምህርትን ሲያስተምሩ ና ቤተ ክርስቲ ያኗን ሲንዱ ነበር:: AD 2000 የተባለውም ድረ ገጽ ይህንኑ ኩነት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል::
“Orthodox hierarchy
has refused the group permission to meet in churches or address congregations. The group doesn’t want to leave
the Orthodox Church but to bring reforms and help people move beyond nominalism
and experience a vibrant relation with Christ “[vii]
ይሄው ስውር የ”ተሐድሶ” ቡድን ግን
እንዳሰበውና እንደታዘዘው የተዋሕዶ ወጣቶችን በጅምላ ወደ ሚሲዮናውያን ጎራ መውሰድ አልቻለም:: ለዚህም ዋናው ምክንያት "ሀይማኖት እንዳባቶቻችን ጥበብ እንደጊዜአችን" በሚል መንፈስ ፣ወጣቱ በዘመናዊው ጥበብ እንዲበረታ ነገር ግን ያባቶቹን ተዋሕዶ ሃይማኖትን ግን ሳይበርዝና ሳይከልስ እንዲከተል ሌት ተቀን የሚጥረው ማኅበረ ቅዱሳን ነበር:: እንዳሰበው እንዳይንቅሳቀስ ዋነኛ ጋሬጣ የሆነበትን ማኅበረ ቅዱሳንን ካላፈረሰ የትም እንደማይደርስ የተረዳው የሄው የ”ተሐድሶ” ቡድን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፈራረስ ያስችለኛል የሚለውን ሁሉ ሴራ ጎንጉኖ አስፈላጊውን ዝግጅት ካደረግ በኋላ ላይ ግልጽ ትንኮሳና ሴራ ጀመረ::
ማኅበረ ቅዱሳን
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር ተዋቅሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተቀመጠለት መተዳደርያ ደንብ መሰረት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ማኅበር ነው::[viii] ይሔው ማኅበር ወደ 80 ሺህ የሚጠጉ አባላት ሲኖሩት በሰሜን አሜሪካ፣ ዩሮፕ ፣እስያ ፣በርካታ ያፍሪካ ሀገራት ቀጠናና ንኡስ ማእከላት አሉት:: ይሄው ማኅበር በአለማችን ላይ ካሉት ጠንካራ ከሚባሉ ክርስቲያናዊ ማኅበራት አንዱ ነው:: Big dreams, Tough reality : Ethiopia
students at crossroads በሚለው ጽሑፉ
ላይ Peter
Lemiuex ማኅበሩን
እንዲህ ሲል ይገልጸዋል::
“the Ethiopian Orthodox student association Mahibere
Kidusan, or “Fellowship of Saints,” which holds weekly meetings such as this
one. Organized under the Sunday School Department of the Ethiopian Orthodox
Church, Mahibere Kidusan has chapters in some 20 universities across Ethiopia
as well as in other African countries, in Europe and in the United States. Some
80,000 Ethiopian Orthodox students are currently enrolled in its three-year
church education program, which runs parallel to the university’s academic curriculum.
The size and global reach of its deeply committed membership are all the more
impressive since Mahibere Kidusan obtained its official license only 18 years
ago. Almost a testament to its prominence, a nearly finished seven-story
building close to campus will house its headquarters.” [ix]
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ባሉ በያንዳንዱ ዪንቨርስቲዎች
ባሉ ግቢ ጉባአያት እያደረገ ያለውንም
እንቅስቃሴ እንዲህ ሲል ይቃኘዋል።
“Mahibere Kidusan champions the Orthodox faith as a bulwark against
society’s many temptations. More controversially, it views the Orthodox Church
as a bastion of traditional Ethiopian culture and identity — distinct from the
West and the East — that its members should embrace and protect from outside
influences. The message resonates strongly with today’s Ethiopian Orthodox
youth, who bear witness to their rapidly changing society.” [x]
በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የመሸጉ የ“ተሐድሶ” አቀንቃኞችና የማኅበረ ቅዱሳንና ፍልሚያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛዎቹ ወጣቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማኅበረ ቅዱሳን የታቀፉ ናቸው ። በየዩንቨርስቲ ያሉት ወጣቶች ማኅበሩ በሚያካሂዳቸው የግቢ ጉባኤያት የታቀፉ ሲሆኑ በቀጥታ የማኅበሩ አባልና ደጋፊ ናቸው።
በየክፍለ ሀገራቱና ክፍለ ዓለማቱ ያሉ የማኅበሩ አባላት ተቀዳሚ ተልእኮ ደግሞ ባሉበት አጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል መሆን ስለሆነ የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳን አሻራ የሌለበት ሰንበት ትምህርት የለም ማለት ይቻላል ። አብዛኛው ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ባመራር ወይም ባባልነት ማኅበረ ቅዱሳን አለ።
እያንዳንዱ የማኅበሩ አባል ደግሞ ባለበት ወረዳም ይሁን ዞን የማኅበረ ቅዱሳን መዋቅር ስላለና ባለበት ሰንበት ትምህርት ቤት ያለውን ሁኔታ በንቃት በመከታተል በወረዳው ወይም በዞኑ ላለው የማኅበሩ መዋቅር ስለሚያሳውቅ ማሀበሩና የማኅበሩ አባላት ባሉበት ቦታ ኑፋቄ ማስተማር ፈጽሞ የማይታለም ነው። ይህ ደግሞ ወጣቱን ከተዋሕዶ ትምህርት የራቀ ትምህርተ ሃይማኖት እያስተማረ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እንዲያምጹ ውስጥ ውስጡን ለሚሰራው የ”ተሐድሶ” ቡድን ከባድና
የማይገፋ እንቅፋት ሆነን የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳን
መሰረታዊ ልዩነት ፣ ከ”ተሐድሶ” ወገኖች በግልጽ
እንደተቀመጠው አንድ ነው ። ይሄንኑ ጉዳይም
Rightside news ባንድ
ወቅት ባቀረበው መሰረት የለሽ ክስ ላይ እንዲህ ሲል አስነብቧል፦
“a group within the EOC called "Mahibere Kidusan"
("Fellowship of Saints") had incited members to …. The increasingly
powerful group's purpose is to counter all reform movements within the EOC and
shield the denomination from outside threats.”[xi]
ይሄው የ”ተሐድሶ” ቡድን ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሶ ማኅበሩ የሚመራቸውን ግቢ ጉባኤያት
ለመረክብ መጀመርያ ማኅበሩን ማፍረስ በሚል ዓላማ በተለይ ላለፉት ሁለት አመታት ማኅበረ ቅዱሳንን በመንግስት አካላትና አባ
ሰረቀ ብርሃንን በመሳሰሉ የውስጥ አርበኞች ለማስመታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም::ይልቁንም የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ
ማኅበሩ ላደረጋቸው አስተዋጾዎች ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ የአዝ ሰንሰለቱም ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ወጥቶ
ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ እንዲሆን ወስኗል:: የማኅበሩም ከሳሽ የነበሩትን ምስጢረ ብዙ የውስጥ አርበኛ
አባ ሰረቀ ብርሃንንም ልዩ ምርመራ እንዲካሄድባቸውና ከዚህ በፊት ጽፈውት ለነበረው በኑፋቄ ለተበከለው የሊቃውንት ጉባኤ መልስ
አንዲያዘጋጅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን ሌሎችም የ”ተሐድሶ” የውስጥ ሴረኞችን በማውገዝ ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለተኛ ግዜ የ”ተሐድሶ” ን
ቅስም በመስበር ታሪካዊ ሥራ ሰርቷል[xii]::
ማኅበረ ቅዱሳንን ማፍረስ
ህልም አንደሆነ የተረዳው ይሄው ራሱን “ተሐድሶ” እያለ የሚጠራው
ቡድን ተሳዳቢ ምላስ ወደ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዞሯል:: የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትንና የቤተ ክርስቲያኒቷ ዓምድ የሆኑት ጳጳሳት
ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀምሯል:: ዋናው ዓላማም ሕዝቡ በጳጳሳቱ ላይ ያለውን እምነትና አክብሮት እንዲያጣና በምሬት
ከቤተ ክርስቲ ያኗ እንዲርቅና በምነታቸው የጸኑትን ሊቃነ ጳጳሳት ታሪክ መንፈሳዊ ወኔና ጥንካረ ለመስበር ታልሞ ነው:: በህይወት የሌሉትን አቡነ ሚካዔል በህይወት ካሉትም እነ አቡነ አብርሃም
አቡነ ሳሙኤል ... ላይ የጳጵሳቱን ስም የሚያጠፉና ሥነ ምግባር የጎደለው የሐሰት ክስ የያዙ መጻሕፍት ታትመዋል::
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ አበው ባሁኑ ወቅት ግልጽ የሆነ ጉዳይ አለ-- የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከባድ አደጋ ውስጥ ናት:: ቤተ ክርስቲ ያኗ ከውስጥና ከውጭ በሁለት ወገን እየተፈተነች ነው:: ባንድ
ወገን ሲኖዶሱ ለሁለት ተከፍሎ አቅሟን አዳክሞታል:: ይሄንኑ ምክንያት በማድረግም በተለይ በውጭ ያለው ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
ለሶስት ተከፍሏል:: የገዥውም ሆነ የተቃዋሚው ፖለቲካ አቀንቃኞች ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በመግባት አጀንዳዎቻቸውን ለማስፈጸም እየሮጡ
ነው:: በዚህ ላይ የፓትርያርኩ ያባ ጳውሎስ አምባገነንነት ተጨምሮበት ቤተ ክርስቲ ያኗን እያዳከማት ነው:: ይሄን አጋጣሚና ክፈተት
በመጠቀምም ራሱን “ተሐድሶ” የሚለው ቡድን ቤተ ክርስቲያኗን ክፉኛ
እየወጋት ነው::ቤተ ክርስትይኗ ከላይ በፖለቲከኞች ከስር ደግሞ በውስጥ ቀበኞች ሁለት እሳት እየነደደባት ነው:: የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተ ክርስቲያን የማፈራረስና ሰላም የመንሳት ሴራ ማብቂያው
መቼ ይሆን?
ይቆየን
[iii]
No comments:
Post a Comment