(አንድ አድርገን ነሐሴ 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በመንበረ ፓትርያርክ የሀዘን የክብር መዝገብ ተዘጋጅቷል ከ12/12/2004 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያ በብጹ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እረፍት የተሰማውን ስሜት በጽሁፍ ማስፈር ይችላል ተብሏል፡፡
የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት እለት ነሐሴ 17/2004 ሀሙስ ከቀኑ 6.00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መሆኑ ተገለፀ:: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቋሚ ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ:: ቅዱስነታቸው 16/12/2004 ረቡዕ ከሰባት ላይ ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስከሬናችው ይሄድና ፍትሃት ሲደረገ አምሽቶ ወደ 11፡00 ላይ በዛኑ ቀን በሰረገላ አስከሬናቸው ሆኖ በብፁዓን አባቶች አጃቢነት ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይገባል ፤ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዚያው ቀን ያድራል ፤
የቅዱስነታቸውን ነፍስ በመንግስተ ሠማያት ያሳርፈው አሜን !!
No comments:
Post a Comment