Wednesday, August 8, 2012

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ AUDIO ያዳምጡ



በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ መሆኑን (ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012) ባወጣነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴንከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ያደረሱትን ዜና አንባብያን ትረዱ ዘንድ ከድምጽ መዝገባችን በጥቂቱ እንድትሰሙት ሁለቱን ክፍል እነሆ እንላለን። እነዚህ ካህናት የሚገኙባቸው አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ የ“ስቀለው-ስቀለው” ጉባኤ የሚሰጡትን መልስም እንጠብቃለን። 
(ክፍል አንድ፤ Part 1) 

ክፍል ሁለት ይዞራል።



 (ክፍል ሁለት/Part 2) 


(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012)፦ በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥየሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለ ወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነትጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ ነው። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምንአሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴን ከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክበዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል


ሳይማሩ ምረናል ቁ አቀናል እያሉ ሕዝቡን እየከፋፈሉት ነው የሚሉት ድብቆቹ ካህናት “ማኅበራትም ሆ ሰባያነ ወንጌል ሀገረ ስብከቱ ሳያውቅና የፈቃድ ደብዳቤ ሳይዙ በየትኛውም  ቤተ ክርስቲያን እንዳይሰብኩ በቅዱስነዎ በኩል ጥብቅ መመሪያ ለየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲተላለፍልንማንኛውም ሰው ወይም ማኅበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ምንም ይነት ፈቃድ እንዳይሰጥ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለአሜሪካን መንግሥት መመሪያ እንዲተላለፍልን ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩን በጥብቅ ማሳሰባችውን የተረቀቀው ደብዳቤ ይገልጣል። የዚህ የድብቅ ካህናቱ ስብሰባ ከተጀመረ አምስተኛ ሣምንቱን አስቆጥል።

ይህን የ“ስቅሎ-ስቅሎ” ድብቅ ስብሰባ በግንባር ቅደምትነት ያስተባበሩትና በማስተባበር ላይየሚገኙት
1.   በላስ ቬጋስ የሐመረ  ኪዳነ ምረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑትና  በአሁኑሰዓ በአቡነ ፋኑኤል የአሪዞና ኔቫዳ እና ዪታ ስቴቶች  ሊቀ ካህናት ተብለው የተሾሙት መልአከ ኪዳን ቀሲስሙኤል ደጀኔ
2.   መልአከ ሰላም አባ ወልደ ሰማዕት ገብረ ሥላሴ (በሲያትል ዋሽግተን የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልአስተዳዳሪና በአቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ስቴት ሊቀ ካህናት ብለው የተሾሙ
3.   መጋቤ ሐዲስ ቀሲስ ዘሚካኤል ታደሰ በሲያትል የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ በአቡነ ፋኑኤልየዋሽንግተን ስቴት ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ ብለው የተሾሙ
4.   ሊቀ ማዕምራን ለይኩን ተስፋ በቴክሳስ ኦስተን የደብረ ኃይል ቅዱስ ኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪበአቡነ ፋኑኤል የቴክሳስ ስቴት ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ ብለውየተሾሙ
5.   ሊቀ ማዕምራን ሞገስ እጅጉ በቴክሳስ ዳላስ የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በአቡነፋኑኤል የቴክሳስ ስቴት ሊቀ ካህናት ብለው የተሾሙ
6.   ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ታደሰ አርአያ በቴክሳስ ዳላስ የደብረ ሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በአቡነ ፋኑኤል የቴክሳስ ስቴት ቤተክህነት ጸሐፊና ሒሳብ ሹም ብለው የተሾሙ
7.   አባ ገብረ ኪዳን ተጠምቀ የሳክራሜንቶ ሐመረ  ኪዳነ ረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በአቡነፋኑኤል በካሊፎርኒያ ስቴት  የኦክላንድ ሳንሆዜና ሳክራሜንቶ ከተሞች ሊቀ ካህናት ብለው የተሾሙ
8.   መልአከ ገነት አባ ገብረ እግዚአብሔር ወልዱ ሳን ሆዜ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንአስተዳዳሪ በካሊፎርኒያ ስቴት በአቡነ ፋኑኤል የኦክላንድ ሳንሆዜና ሳክራሜንቶ ከተሞች ቤተ ክህነትየስብከተ ወንጌልና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ ብለው የተሾሙ
9.   መልአከ ሰላም አባ ገብረ ማርያም  ታፈረ የሳንዲያጎ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንአስተዳዳሪ በአቡነ ፋኑኤል በካሊፎርኒያ ስቴት  የሎሳንጀለስ፣ የሳንዲያጎና የፍሬዝኖ ከተሞች ቤተ ክህነትየስብከተ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኃላፊ ብለው የተሾሙ
10.  መልአክ መዊዕ ቀሲስ ኃይለ ኢየሱስ ዱሬሳ የደብረ መዊዕ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይበአቡነ ፋኑኤል የአሪዞና ኔቫዳ እና ዩታ ስቴቶች ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኃላፊብለው የተሾሙ
ሲሆኑ የሌሎችንም ካህናት ስም ዝርዝር በቀጣይ የምናጣ መሆኑን ቃል እንገባለን።

የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ጁላይ 1/2012  ሲያደርጉ በስብሰባው እንዲገኙ ለጠሯቸው ካህናት የስብሰባውንላማና ግቡን  ሲያብራሩ እንደ ማደናገሪያነት የተጠቀሙበት  ከቅዱስ ፓትርያርኩ የሚላ መመሪያዎችና ትዕዛዞችን እን ማስፈጸም እንችላለን የሚል ነበር። ብዙ ሳቦችንም ካብላሉ በኋላ ኮሚቴ መርጠውተለያይተዋል።  የኮሚቴው  ሰብሳቢም መልአከ ሰላም አባ ወልደ ሰማዕት የሲያትል ደብረ ሰላም ቅዱስሚካኤል አስተዳዳሪ ምክትል ሰብሳቢ ሊቀ ማዕምራን ለይኩን ተስፋ ከኦስተን ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፣ሐፊ ደግሞ ሊቀ ሥዩማን ቀሲስ ታደሰ ከዳላስ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሲሆኑ ስብሰባውምለቀጣይ እሑድ ጁላይ 8/2012 ሰባት ሰዓት ላይ ቀጥረው አልፈዋል። ይህንንም ስብሰባ በማስተባበርናበማደራጀት ለየካህናቱ ስልክ በመደወል ዓቃቤ ሰዓት በመሆን ያለመሰልቸትና ለዚህ እኩይ ተግባር በመትጋትበዋናነት የሚጠቀሱት የላስ ጋሱ መልአከ ኪዳን ቀሲስ ሙኤል ደጀኔ ናቸው።

የሁለተኛው ስብሰባም ጁላይ 08/2012 ቀን በምዕራብ አሜሪካ ፓሲፊክ ሰዓት አቆጣጠር 700 .ኤም ላይየጀመሩ ሲሆን በዚህ ቀን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ (የሰብሳቢዎቹን እኩይ አላማ ባለመረዳትከላይየተጠቀሱ አስተባባሪዎቹን ጨምሮ ወደ 16 የሚጠጉ ካህናት ተገኝተው ነበር። ስብሰባው በቴክሳስ ዳላስ አብያተክርስቲያን ሦስት ጊዜ የከፋፈሉ መሆናቸው በሚነገርላቸው በሊቀ ማዕምራን ሞገስ እጅጉ ቀልድና ነገረ ዘርቅ ተጀምሯል። ከዚያም ሊቀ ስዩማን ቀሲ ታደሰ አርአያ ከፓትርያርኩ የሚመጣን መመሪያ ማስፈጸም እንት እንችላለን? በአቡነ ፋኑኤል ላይ የተቀጣጠለውን ተቃውሞ እንዴት ማቀዝቀዝ እንችላለን፣ ስማቸውንበመጥራትና ባለመጥራት ጉዳይ ላይ እን አድርገን እናስተካክለው? አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትፓትርያርኩን ስም እን የአቡነ ፋኑኤልን ስም በጸሎተ ቅዳሴ አናነሳም የሚሉ አሉ ምን እናድርግ? የሚልሳብ ለጉባኤው አቅርበዋል


ይህ ንዲህ እንዳለ ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዛሬ ለስብሰባው የመጀመሪያቸው እንደሆነና በመጀመሪያየካህናት መሰባሰብ ተገቢና ቅታዊ እንደሆነ እስከ አሁንም መቆየታችው ጥሩ እንዳልነበረ ገልጸው መጀመሪያግን ወደ ረታዊ ሳቡ ከመግባታችን በፊት እኛ (ስብስቡ) ማን ነን?” የሚለው ጥያቄ ጠይቀዋልቀጥለውም “ዋስትናችንስ ምንድን ነው?” ብለዋል። ይህንንም አባ ወልደ ሰማዕት ሲያብራሩ ዋስትናችን አንድነታችን ነው ብለው መልሰዋል። ከዚያም  “እኛ ማን ነን?” ሲሉ ለጠየቁት ራሳቸው ሊቀ ክህናት መልሱመተዳደሪያ ደንብ ኑረን፣ አወቃራችን ከቃለ አዋዲው ውጭ ለሆነ የራሳችንን ህልውና ማረጋገጥስለላለብን ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረን ያስፈልጋል ብለዋል። ማብራሪያ ሐሳቡን ሌሎቹ ተሰብሳቢዎቹተቀብለውታል።

ስያሜ ምን መሆን እንዳለበት ቅድሚያውን የወሰዱት ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ሲያብራሩም በረ ካህናትብንለውና ደንብ ቢኖረን ጥሩ ነው ብለዋል አንዳንዶቹ ተሰብሳቢዎች “ይህ ስብስብ ከሀገረ ስብከት የተለየበር ስለሆነ ደንብ ቢኖረን የተቀረጹትን አጀንዳዎች ብንወያይበት ጥሩ ነው ብለው ጥያቄ  አቅርበዋል።ሰብሳቢውም የሊቀ ካህናት ጥያቄ  ጥሩ እንደሆነና እኛን ሀገረ ስብከቱ ቢቀበለን የሚል ሃሳብ አቅርበው አጭሩመንገድም በሀገረ ስብከቱ ስር መቋቋም እንደሆነ ጠቁመው አልፈዋል። ከተሰብሳቢዎቹም መካከል በኩረ ትጉሃን አቡሃይ ለመሆኑ ይህንን ስብስብ ሊቀ ጳጳሱ ያውቃሉ ወይ?” ብለው ጠይቀው ሰብሳቢውም ሲመልሱ ለሊቀጳጳሱ ነግረናቸው ተቀብለውት በርቱ ብለውናል በማለት ገልጸዋል።

ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ሃሳብ ረት ጉባኤው የመተዳደሪያ ደንቡን የሚያረ ሰዎችእንዲመርጥ ተስማምተው የሚከተሉት ሰዎች ተመርጠዋል።
1.      መልአከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ
2.     ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ
3.     ሊቀ መዘምራን ክነፈ ርግብ ሐጎስ
4.     በኩረ ትጉሃን አቡሃይ ፈንቴ እና
5.     መጋቤ ምሥጢር በቃሉ ከሃሊ

ይህንንም ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ተሰብሳቢዎቹ በሙሉ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያለውን ችግር  ይዘው መጥተውለአርቃቂ ኮሜቴው የመነሻ ሳብ እንዲሆነው በሚል ስማምተው ተለያይተዋል።

በሶስተኛው ቀን ማለትም በጁላይ 15/2012 ስብሰባቸው ላለፉት ሁለት ሳምንታት በተሰበሰቡበት ኮንፍረንስ ሩም አልነበረም የተሰበሰቡት የኮንፍረንሱ ሩም የመግቢያ ቁጥር ስለተቀየረ ወደ አዲሱ ሩም ገብተዋል። ስብሰባውም የተጀመረው ባለፈው ሳምንት የተሰጣቸውን የቤት ሥራ ሁሉም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያለው ችግር ምን እንደሆነ ይዘው እንዲመጡ ስለነበር  ሁሉም  በዋናነት እንደ ችግር አደገኛ ጉዳይ እና ቤተ ክርስቲያን ራሽ አድርገው ያቀረቡት በረ ቅዱሳንን በረ  ወልድ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንነበር።

በዚህም ከተወያዩ በኋላ ለአርቃቂ ኮሜቴው ሳባውን ገልጸውና በደንብ እንዲብራራ አድርገው ደንብ ለሚያረቁት የመነሻ ሳብ ያህል በቂ እንደሆነ ተደርጎ ተወስል። ለቀጣይም ለቅዱስ ፓትርያርኩ በአድራሻ ስልሚጻፈው ደብዳቤ ብዙ ውይይቶች ተደርገው ደብዳቤውን የሚቁ ሰዎች መርጠው ለቀጣዩ ሳምንት ይዘው እንቀርቡ ተስማምተዋል። እንዲሁም ከዚህ በፊት ያልገቡ ካህናትን ማነጋገርና ማሳመን እንዳለባቸውተወያይተውና የሚያነጋግሩ ሰዎችን መርጠው ሰይመዋል።

እንደተባለውም በጣዩ ማለትም በአራተኛው ሳምንት  ስብሳባ ላይ ባለፈው ሳምንት የተሰጣችውን የቤት ሥራ በመጀመሪያ ሪፖርት እንዲያደርጉ ከዚያም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ስለሚላከው ደብዳቤ ረቂቅ ውይይት እንዲደረግ ሰብሳቢው አባ ወልደ ሰማዕት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። ካህናትን ነጋገርን በተመለከተ አባ ገብረ ኪዳን ተጠምቀኦክላንድ እና ሳንሆ ያሉ ካህናትን እንዳነጋገሩ፣ መልአከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል  አንጀለስ ቅድስት ሥላሴያሉ ካህናትን እንዳነጋገሩ፣ በኩረ ትጉ አቡሃይ ኦሪጎን ያሉ ካህናትን እንዳናገሩ ጥቅሰዋል። በዚህምካነጋገሯቸው አብያተ ክርስቲያናት አባቶች ያገኙትን አሉታዊና ንታዊ መልስ ለተሰብሳቢዎቹ  ገልጸዋል።

በመቀልም  በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያለውን ወቅታዊ ችግር  ሪፖርት አድርጉ በተባሉት ረትየመጀመሪያውን ሪፖርት ያቀረቡት የአሪዞናው ቀሲስ ይለ ኢየሱስ ሲሆኑ ያለባቸውን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንችግር አብራርተዋል ሀገረ ስብከቱ የላከውን ደብዳቤ አልተቀበሉትም እኔም እስካሁን በአየር ላይ ነው ያለሁት የሊቀ ጳጳሱንም  ስም አልጠሩም በማለት ገልጸዋል። ከዚያም በመቀጠል የላስ ቬጋሱ ቀሲስ ሳሙኤልደጀኔ ጁላይ 26/2012 በተደረገው የቤተ ክርስቲያኒቱ  ምዕመናን ቅላላ ጉባኤ ላይ የነበረውን ደት ሪፖርትሲያቀርቡ ቤተ ክርስቲያኒቷም እስከ አሁን ድረስ አቡነ ፋኑኤልን እንደማትጠራና የርሳቸውንም ሐሳብ ሕዝቡ በስብሰባ ወቅት ውድቅ እንደረገባቸው ጠቅሰው አሁንም ግሩፕ በሆነ አካሄድ የሊቀ ጳጳሱን ስም ላለመጥራት ወስነዋል (ሕዝቡ) ፍትሐ ነገሥት እየተጠቀሰ ሲብራራለት ውሎአል ብለዋል።

በመካከሉም የኦክላንዱ ቀሲስ ሞላ ውቤ የት ነው እሱ እንህ የተደረገው?” ብለው ሲጠይቁ ላስ ጋስ ነውብለው ሲመልሱም አብሮዎት ያሉ ካህን ማን ይባላሉ?” በማለት በድጋሜ ቀሲስ ሞላ ጠየቁ መልአከ ሳሌም አባ ገብረ ኪዳን ናቸው እንደ ፕሬዝዳንት ኦባማ በጣም ብዙ ጊዜ ሲያስጨበጭቡ ነው ያመሹት በማለት አብራርተዋል የነገር ቁና በመተብተብ ታዋቂው ሊቅ ሞገስ እጅጉ ምን ገብረኪዳን ነው (ገብረ ከዳን) ነው እንጅ በማለት በመሳለቅ ጉባኤው ሳቅ በሳቅ አድርገውታል፡፡ ቀሲስ ሳሙኤልም ይህንንም የዕመናኑን ጉባኤቪዲዮ እንደቀረጹትና አስፈላጊ ከሆነም ለዚህ የካህናቱ ጉባኤና ለፓትርያርኩ ሊልኩ ዝግጁ እንደሆኑአስረድተውል። በተያያዥም ሊቀ ጳጳሱን የተቃዎሙትን ካህናት ስም ዝርዝር ከዌብሳይት ላይ ፕሪንት እንዳደረጉት እና ለቅዱስ ፓትርያርኩ ከደብዳቤው ጋራ አያይዘው እንደሚልኩት ለካህናቱ ጉባኤ ገልጸዋል።

ይህንን ጁላይ 29/2012 የተደረገውን ጉባኤ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴለማየሁን ጨምሮ በርከት ያሉ ካህናት አለመግባታቸው ነው። በውይይቱ ወቅትም ለፓትርያርኩ በአድራሻየተጻፈው ባለ ስምንት ነጥብ የክስ ደብዳቤ ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ማኅበረ ቅዱሳንን ማኅበረ በዓለወልድን እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤን  እንዲሁም  ባሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያንን በመዋጋት ላይ ያሉትን የመናፍቃን ሴራ በማጋለጥ መልስ በመስጠት እንዲሁም ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ ለሕዝቡ በማቅረብ ላይ ያሉትን ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር ሔርንና ደቄቀ ናቡቴንከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር የሚያወግዝ ነው። በስብሰባው ላይ ቄስ ፍስሐ የተባሉት ተሰብሳቢ ስለአባ ሰላማ ብሎግ ሲያብራሩ እነሱ የመናፍቃን አሉት እንጅ እኔ በበኩሌ አላምንበትም (የመናፍቃን አልለውም)” ሲሉ የካህናቱ ጉባኤ ነውም አይደለምም ሳይል ዝም ብሎ ማለፉ አስገራሚ ሆኗል።

ይህ የሚሳየን የዚህ የካህናት ስብሰባ ዓላማ ለቤተ ክርስቲያኒቱ በመቆርቆር ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳንን እና መሰል ማኅበራትን እንት ማፍረስ እንዳለባችው ለመዶለት በመሆኑ እንጂ ቄሱ የተናገሩት ነገር የሚታለፍ ሆኖ አልነበረም። በመሠረቱ ደጀ ሰላም የካህናትን መሰብሰብ እና ስለ መብታቸው እና ስለ አገልግሎታቸው መመካከር በጽኑዕ ትደግፋለች። “ስቅሎ ስቅሎ” (ስቀለው ስቀለው) ለማለት ብቻ መሰብሰብ ግን ጌታን ከሰቀሉት አይሁድ ይደምራቸው ካልሆነ ከእውነተኞቹ አበው ጎራ አያሰልፋቸውም። ዛሬ አቡነ ፋኑኤልን እና የአባ ሰላማን ጥምረት ከምእመናን ቁታ ለማዳን እንደተሰባሰቡት በመናፍቃን እና በአረማውያን እንዲሁም በሙስና በተዘፈቁ መሪዎቿ የሚደርስባትን መከራ ቀንበር ለማቅለል ምንም ፍላጎት የሌላቸው ሆነው መገኘታቸው በእጅጉ ልብን በሐዘን ይሰብራል።

በስብሰባው መካከል አንዱ የውይይት ሐሳብ አቅራቢ ሲናገሩ እንደሰማነው እና የመከራከሪያ ነጥብ አድርገው ያቀረቡት ደጀ ሰላም ስለ ቅ/ፓትርያርኩ የዘገበችውን አዲሱን የስማቸውን ቅጥያ መጠቀም እና አለመጠቀምን በተመለከተ ነው። የዚህን ከሥርዓት ውጪ የሆነ የፓትርያርክ ስም ጋጋት እንደ ቁምነገር ቆጥረው መነጋገሪአ ማድረጋቸው እንኳን በእነርሱ ደረጃ በሚንቋቸው በሰንበት ት/ቤቶች ደረጃም የሚሆን አለመሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም።

ወቅቱም በተለይም እነዚህ ካህናት በሚገኙባቸው የአሜሪካ ስቴቶች የሚገኙ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች እንዱሁም ሰበካ ጉባኤዎች ስለ እነርሱ ምን እንደሚሉ እና ምን እንደሚያስቡ ማወቅ ይኖርባቸዋል። ሰንበት ተማሪዎቹንም ሆነ ሌሎቹን ምእመናን ለቤተ ክርስቲአናቸው ምንም እንደማያገባቸው፣ ገንዘብ አምጡ ሲባሉ ብቻ ማምጣት እንዳለባቸው፣ ካሱ ኢላላ ስለ ኢትዮጵያው ቴሌ እንዳሉት “የሚታለቡ ላሞች” አድርገው መውሰዳቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። አሁንም እንላቸዋለን ሃይማኖትን በተመለከተ ምእመን የለም፣ ዲያቆን የለም፣ ቄስና ጳጳስ የለም ሁሉም ያገባዋል። ሁላችንም ያገባናል። ምእመኑም፣ እናንተ እንዳላችሁት “የሚታለብ ጥገት ላም” አይደለም። ገንዘቡን እንደምትፈልጉት እርሱንም መፈለግ ይገባችሁ ነበር።

ማስታወሻ፦ የአምስቱንም ሳምንታት ስብሰባ ሙሉ ውይይት ማስረጃ በእጃችን አለን። እንደ አስፈላጊነቱ በድምጽ የምናቀርብላችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

የቤተ ክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ። አሜን

ቸር ወሬ ያሰማን።

No comments:

Post a Comment