- አዲሱ አስተዳዳሪ ሰበካ ወንጌሉንና ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሰብስበው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ሰው እዚህ ቤተክርስትያን መጥቶ እንዳያገለግል የሚል መመሪያ ሰጥተዋል
(አንድ አድርገን ነሐሴ 2 2004 ዓ.ም)፡- ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው በባቦጋያ መድኃኒዓለም የጥምቀት ታቦት ማሳደሪያ ቦታ ላይ ከባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት ከአቶ ታዲዎስ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ገልጸን በየጊዜው መረጃ በብሎጋችን ላይ ማውጣታችን ይታወቃል ፤ በአዲሱ የባቦጋያ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፤ በአቶ ጌታቸው ዶኒ እና በሪዞርቱ ባለቤት ጠበቃ አማካኝነት በተሸረበ ክስ ከ13 በላይ ስለ መድኃኒዓለም ቦታ ዘብ የቆሙ ክርስትያኖች ሰኔ 19 2004 ዓ.ም መታሰራቸው ይታወቃል ፤ እነዚህ ሰዎች ላይ ያለአግባብ በሪዞርቱ ባለቤት እና በጌታቸው ዶኒ የሀሰት ክስና የሀሰት ምስክርነት መሰረት 7 ወር ተፈርዶባቸው መታሰራቸውን በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ በጊዜውም የተፈረደውን ፍርድ በርካቶች የተቃወሙት ሲሆን ፖሊስ ከፍርድ ቤት የማሰሪያ ትእዛዝ አውጥቶ ሰዎቹን ይዙ በሚሄድበት ጊዜ ከ400 የማያንስ ምእመናን ወደ እስር ቤት በእንባ ሸኝቷቸዋል ፤
እነዚህ ሰዎች ከታሰሩ በኋላ ከደብረዘይት አዳማ ከተማ ድረስ ያለመሰልቸት ለተከታታይ ሳምንታት በአንድነት በመሆን በርካታ ምዕመናን ጠይቀዋቸዋል ፤ ይህ እንዲህ እያለ በጊዜው ያለአግባብ የተፈረደባቸው እስረኞች ለምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይግባኛቸውን በአግባቡ መመልከት አልቻለም ነበር፤ ከበታች ፍርድ ቤት ፍትህን ያጡ እነዚህ ወገኖች የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችሎት ይግባኛቸውን ያቀረቡ ሲሆን ይግባኙ ከቀረበበት በሶስት ቀጠሮ ሰዎቹ ላይ የተፈረደው ፍርድ ህግን ያልተከተለ እና ግልጽነት የጎደለው ፤ የግለሰቦች ሃሳብ መሰረት ያደረገ መሆኑን ካስረዳ በኋላ የአደአ ፍርድ ቤት ሰኔ 19/2004 ዓ.ም ለ7 ወር የፈረደባቸውን ሰዎች በድፍን አንድ ወሩ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመከበር ላይ ሳለ ሐምሌ 19 /2004 ዓ.ም በነጻ ከእስር ተለቀዋል፡፡
በወቅቱ ያለአግባብ ለባለሀብቱ የተሰጠው ከ10ሺህ ካሬ በላይ የጥምቀትና ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ ላይ የነበረውን መስቀል እንደ ተራ ነገር ያስቆረጡት ቀስሲ መስፍንና ለዚህ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ይሆነው ዘንድ በአስር ሺዎች ብር ከሪዞርቱ ባለቤት የተመደበለት የነበረው አቶ ጌታቸው ዶኒ ከባለሃብቱ ጋር በመመሳጠር አስተዳዳሪውን በመያዝ እንዳስቆረጡት ይታወቃል፡፡ ህዝቡም ይህ መስቀል ያለአግባብ ከተቆረጠ በኋላ ለምን? ብሎ ሲጠይቅ በአስተዳዳሪው የተሰጠው መልስ ቢኖር “መስቀል ምን ያደርጋል እንጨት ነው ዝም ብላችሁ አትጩሁ” የሚል ሲሆን ይህ መልስ ህዝቡን በማስቆጣቱ የቀድሞ የባቦጋያ መድኃኒዓለም አስተዳዳሪ ቀስሲ መስፍንን አቡነ ጎርጎርዮስ ከደብሩ በማንሳት ወደ ደብረ ዘይት ቃጅማ ደብረ ገነት በአስተዳዳሪነት ቦታ ቀይረዋቸዋል፡፡
እኝው የአቶ ጌታቸው ዶኒ ባለውለታ ወደ ደብረ ገነት ተቀይረው ወር ሳይሞላቸው ሐምሌ 24/2004 ዓ.ም ቃጅማ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ስብከተ ወንጌል ባዘጋጀው የህዝብ ጉባኤ ላይ የተጋበዙትን መዘምራንና እንዳያገለግሉ አግደዋችዋል፡፡ በወቅቱ ስብከተ ወንጌሉ እና ሰ/ት/ቤቱ አብረው በዚህ ሁኔታ ወደፊት መቀጠል እንደማይችሉ በግልጽ ነግረዋቸዋል፡፡ በጊዜው ህዝቡም ተቃውሞውን ሲገልጽና መዘምራኖቹ ለምን እንደታገዱ ሲጠይቅ እንደነበር ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
ዘማሪዎቹ ከአዲስ አበባ የመጡ ሲሆኑ እነሱን በመሳሪያ የሚያጅበው ወንድም ደግሞ የባቦጋያ መድኃኒዓለም የመሬት ጉዳይ የህግ ጠበቃ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ፤ በተጨማሪም አዲሱ አስተዳዳሪ ሰበካ ወንጌሉንና ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሰብስበው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ሰው እዚህ ቤተክርስትያን መጥቶ እንዳያገለግል የሚል መመሪያ እንዳስተላለፉላቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጊዜው የእግዚአብሔርን ቃል ለምዕመና ያስተላለፈው ዲ/ን ተስፋዬ ሞሲሳ የተሀድሶ ክንፍን በመቃወም የሚታወቅ ሰባኪ ወንጌል ሲሆን ይህን አቋሙን የሚያውቀው ከተሀድሶያውያን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሰራውበጠቅላይ ቤተክህነት የሚገኝው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ መምህር አመረ አሸብር አማካኝነት የማገልገል ፍቃድ ስለተከለከለ ማገልገል በፈለገበት ቦታ ከደብር አስተዳዳሪዎች ጋር በመመሳጠር እንዳያገለግል እንቅፋት እየሆነው ይገኛል ፤ በየቦታው እኒህን የመሰሉ ወንድሞች ላይ ቀድሞ አገልግሎታቸውን በማደናቀፍ መምህር አመረ አሸብር የውስጥ እሾህ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
አሁንም በቦታው የሚገኝው ምዕመናን ጥያቄ አንድና አንድ ነው “ያለ አግባብ የተሸጠው ቦታ ይመለስ” የሚል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት የቦታዉ ጉዳይ ዳግም በሕግ እየታየ ይገኛል ፤ አቡነ ጎርጎርዮስም ከሕዝቡ ጋር መታረቅናመነጋገር እንደሚፈልጉም የገለጹ ሲሆን ከእስር በተለቀቁት ክርስቲያኖች መታሰር ዙሪያ ግን ፍጹም እጃቸዉእንዳሌለበትና ጉዳዩንም እንደማያዉቁት ለምዕመኑ ተናግረዋል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
No comments:
Post a Comment