(አንድ አድርገን ሰኔ 18 2004 ዓ.ም)፡- ቀኑ እለተ ሰንበት ሰኔ 17 2004 ዓ.ም ፤ ሰንበት እንደመሆኑ የት ሄጄ እንደማስቀድስ ሳወጣ ሳወርድ ውስጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያር ገዳም ቤተክርስትያን እንድሄድ አመላከተኝ ፤ ቦታው ጦር ኃይሎች ወደ ወይራ-ቤተል ሲሄዱ አጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ የምትገኝ ቤተክርስትያን ናት ፤ በጣም በጠዋት በመነሳት ካህናት ቅዳሴ ሳይገቡ ለመድረስ ተጣደፍኩኝ ፤ እንደ ሃሳቤም ተሳቶልኝ ቅዳሴ ሳይገቡ መድስረስ ቻልኩኝ ፤ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ደስ በሚያሰኝ እኛ ውስጥን ሀሴት በሚሞላ መልኩ ቅዳሴው ተጠናቀቀ ፡፡ ከዚያ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ የቀኑ ተዓምረ ማርያም ተነበበ ፤ ምዕመኑ ሁሉ ቆሞ ፍጹም በሆነ ፀጥታ የእመቤታችንን ተዓምር አደመጠ፡፡
Monday, June 25, 2012
የ“አዲስ ራዕይ” አመለካከት (ክፍል 2) ….
ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ
- ከዋህቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚለው በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል
- ኢህአዴግ የቄሱም የሼሁም ድርጅት ነው ፡፡ ከአባልነት አንጻር የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ፡፡ የአንድ እምነት ሰባኪ የሆነ ሰው ኢህአዴግ አባል መሆን ይችላል የኢህአዴግ አመራር መሆንን ግን አይፈቀድም
- ደርግ ግለሰቦችን በተናጠል ሲገድል እናንተ ደግሞ ገዳማትን በማፍረስ በጅምላ እምነትንና አማኞችን የመግደል ምግባር ላይ ተሰማርታችኋል
- በርካታ አባላት ማህበረ ቅዱሳን እንደሆኑት ሁሉ በርካታ አባላትም የወሃቢያ ወይም የሌላ የእስልምና ፈለግ ተከታዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ችግሩ የትኛውም እምነት ይከተሉ የሚለው አይደለም ፡፡ ችግሩ ያለው..............................
(አንድ አድርገን ሰኔ 15 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከትላንት በስተያ በወፍ በረር በመቃኝት “አዲስ ራዕይ” መጽሄትን በጥቂቱ ለማስዳሰስ ሞክረን ነበረ ፤ አሁን ደግሞ ምን አይነት ነጥቦች እንዳካተተ ፤ በየነጥቦቹ ስር ምን ዓይነት ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ለማሳየት እንሞክራለን ፤ የአጻጻፍ ይዘት እና የጽሁፉን ፍሰት አብረን እንቃኛለን፡፡ የራሳችንንም ሃሳብ ጣል በማድረግም እናያለን ፤ ፅሁፉ ሲጀምር “በሰላምና ህገ-መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትም ግዴታም ነው” በማለት ይጀምራል፡፡
በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ
· የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአስተዳዳሪው ላይ ያቀረበው የሙስናክስ በመጣራት ላይ ነበር::
· ወርቅ፣ የውጭ ምንዛሬና የሌሎች ነዋያት ግምት ሳይጨምር በጥሬ ብር ከ200,000 በላይ መዝብረዋል::
· የአስተዳዳሪውን ሹመት በማስፈጸም የእጅጋየሁ በየነ ሚናአለበት::
· የሀ/ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ለዐመፅ ለማዘጋጀት አባ ጳውሎስ ያሰቡት ዕቅድ አካል ይኾን?
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- ሰባኬ ወንጌል ከነበሩበት የመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን ብቻ ነው ያስቆጠሩት - አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ፡፡በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትንጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢየመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነትአስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይአደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።
Friday, June 22, 2012
በጀርመን የቅ/ሚካኤል በዓለ ንግሥ በመናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004
ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- በደመቀ ሁኔታ
ተጀምሮ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ሆን ብለው ከረፈደ በቦታው በተገኙት መናፍቁ «ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ
አበቃ። በሀገረ ጀርመን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኑፋቄያቸው ምክንያት በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቁጣን እያስነሱ ያሉት መናፍቁ
“ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ “ከልካይ የለኝም” በሚል መንፈስ በአካባቢያቸው የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን በአውቶብስ ጭነው ከአካባቢያቸው ወጥተው
በአገልግሎት እንዳይስተፉ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የጣሉባቸውን እግድ በመተላለፍ እሑድ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ
ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።
ላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር አልሠራም አለ
የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር አልሠራም አለ
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ
ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ ምለኩ
በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ
መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።
ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን
እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው
ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና
ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት
ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ
ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል።
በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦ 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ
ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት
የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን
ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ
ይህንን ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜንWednesday, June 20, 2012
ኢህአዴግ “በአዲስ ራእይ” መጽሄት ምን እያለ ነው?
- በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡”
- ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ
- ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው
- ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆየምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡
- በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ .........
- እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው
(አንድ አድርገን ሰኔ 12 /2004ዓ.ም)፡-PART 1
አዲስ ራዕይ በየሁለት ወሩ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡ |
Tuesday, June 19, 2012
አቡነ ጳውሎስ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘ ቡድን እያደራጁ ነው
አርእስተ ጉዳዮች፡- (READ THIS ARTICLE IN PDF)
- · አቡነ ጳውሎስ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መናጋቱ የተረጋገጠውን የዐምባገነንት ሥልጣናቸውን ያድሱልኛል ያሏቸውን ሦስት ቡድኖችን አቋቁመዋል፤ “ጉባኤ አርድእት” አንዱ ነው።
- · የ”ጉባኤ አርድእት” መተዳደርያ ደንብ ከሰሞኑበአቡነ ጳውሎስ ፊርማ እንደሚጸድቅ እየተነገረ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ቢሮ ተሰጥቶታል፤ ምንጩ ያልታወቀ በጀትም ተመድቦለታል፤ 25 መሥራች አባላት እና 180 ተባባሪ አባላት እንዳሉት ተገልጧል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሂደቱን በትኩረት እየተከታተሉት ነው።
- · ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንን ጨምሮ በአእመረ አሸብር፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ እና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራ ነው የተባለው “ጉባኤ አርድእት” የአቡነ ጳውሎስን የጠቅላይነት ሥልጣን የሚያጠናክር የሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹ማሻሻያ› ረቂቅ አዘጋጅቷል፤
- · “ቤተ ክርስቲያን ራሷ ማኅበር ስለሆነች በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም” በሚል እንደ ማኅበረ ቅዱሳን እና የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበርያሉትን ማኅበራት ለማዳከምና ለማፍረስ ይሠራል፤ ይህም ካልተሳካ ራሱን ወደ “ማኅበረ አርድእት” ለውጦ በማኅበራቱ ላይ የማያባራ ቀውስ ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል፤ “ከማኅበረ ቅዱሳን ያኮረፉ” የሚባሉ ሰዎችን ሰብስቦ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥቃት አንዱ ስልቱ ነው፤
- · በሰላም፣ ልማትና ሰብአዊ ተራድኦ ዙሪያ ከተደራጁ የወጣት ማኅበራት ጋራ እሠራለኹ በሚል አባላትን በአፈሳ ለመመልመልና መንግሥትን በማወናበድ የፖለቲካ ድጋፍ ለመሸመት ይጠቀምበታል፤
- · በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠንካራ አቋም የያዙ ብፁዓን አባቶችን በፖለቲከኛነት በመወንጀል፣ በአሉባልታዎች ስማቸውን በማጥፋት፣ በየአህጉረ ስብከታቸው ሁከት በመፍጠር የተቀናጀ የማሸማቀቅ ዘመቻ ይከፍታል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ ሕዝቅኤል፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና አቡነ ገብርኤል የወቅቱ ዒላማዎች ናቸው፤
- · አቡነ ጳውሎስ የግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በአራቱ ቃለ ጉባኤአልፈረሙም፤ ቋሚ ሲኖዶስ ፓትርያርኩ አራቱንም ቃለ ጉባኤ ካልፈረሙ በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እንደማይሰበሰብ በመግለጽ አቡነ ጳውሎስን አስጠንቅቋል፤
- · በአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ “በጄነራል ዳይሬክተር ማዕርግ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት” እንደተሰጠው የሚነገርለት የ”ጉባኤ አርድእት” ቀንደኛ አስተባባሪ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን “ጉባኤ እግዚአብሔር” (Ethiopia Assemblies of God) የተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት እንደሚያዘወትር፤ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነቱ ተወግ የተባረረውን የሃይማኖተ አበው አባላት በጎጠኝነት ስሜት እያነሣሣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ እየዶለተ መኾኑ ተገልጧል፣
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 11/2004 ዓ.ም፤ ጁን 18/ 2012):- ክብር - ሥልጣን - ጥቅም፤ የኻያ ዓመት የአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ራሮት ስለ መኾናቸው ብዙዎች ይስማማሉ፤ ራሮቱ የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶስ አመራርና አሠራር ክፉኛ ከመፈታተኑ የተነሣ “በስም እንጂ በተግባር የሌለ”እስከማሰኘት የደረሰበት ኹኔታ አጋጥሟል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ የአመራርና የአስተዳደር ማእከል የኾነው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በዕቅድና ዕቅዱን በሚደግፍ የሰው ኀይልና በጀት ተደግፎ የሚመራ አብነታዊ ተቋም ሳይሆን የአድልዎ አሠራር፣ የአስተዳደር በደልና የሀብት ምዝበራ መለዮው የኾነ ግዙፍ ግን የበሰበሰ መዋቅር ለመሰኘት በቅቷል፡፡ በአጭር አነጋገር የሚከተለው የአንድ አዛውንት ፖለቲከኛ ቃል ከእንግዲህ ውድቀት እና ውርደት እንጂ ሌላ የመኾን ተስፋ የማይታይበትን የአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና በማጠቃለል ሊገልጸው ይችላል - “ቤተ ክርስቲያኒቱ በጠና ታማለች ካልን አቡነ ጳውሎስ ገደሏት፤ የለም÷ከዚያም በፊት ሞታ ነበር ካልን አቡነ ጳውሎስ ቀበሯት ለማለት እንችላለን፡፡”
ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ
· መናፍቃኑ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም።
· የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ።
· መናፍቃኑ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ።
· ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል።
· ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያርኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
· “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
Friday, June 15, 2012
የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት፣ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በ”ችግር ፈጣሪው” አስተዳዳሪ አባ ሚካኤል ታደሰ ታውከዋል
READ THIS ARTICLE INPDF.
· በአስተዳዳሪነት የተሾሙት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ ዐዋዲውን በመጣስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመኾናቸው ማዕርገ ክህነታቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከተወገዙ በኋላ ነው።
· ሀ/ስብከቱ የሀብት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ ዘረፋን ያበረታታሉ።
· ሰንበት ት/ቤቱን ‹ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው› በሚል አገልግሎቱን የሚያደናቅፉ ርምጃዎች ወስደዋል።
· አስተዳዳሪው ከአባ ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስ ሢመት ተስፈኞች አንዱ ናቸው።
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 8/2004 ዓ.ም፤ ጁን 15/ 2012/) በማዕርገ ዲቁናቸው በእቲሳ ደብረ ጽላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በዐቃቢነት አገልግለዋል፡፡ ያን ጊዜ ስማቸው ዲያቆን ሙሉነህ ታደሰ ይባል ነበር፡፡ በገዳሙ ማዕርገ ምንኵስና ሲቀበሉ ስማቸው አባ ኀይለ ኢየሱስ ታደሰ መባሉን የገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 79/05/98 በቀን 16/05/1998 ዓ.ም የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የግለሰቡን ማንነት አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡
Wednesday, June 13, 2012
የአቶ የጌታቸው ዶኒ ክስና የፍርድ ሂደት
(አንድ አድርገን ሰኔ 06/2004ዓ.ም)፡- በጌታቸው ዶኒ አቀነባባሪነት የባቦጋያ ምስራቀ ፀሀይ መድሃኒአለምን ቦታ አስመላሽ ጥቂት ኮሚቴዎች ላይ “የማስፈራራት ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ሙዳይ ምጽዋት ገልብጠዋል” በማለት አቶ ጌታቸው ዶኒ እና የቤተክርስትያቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው ይታወቃል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ በሀሰት ምስክርነት ያቀረባቸው ሰዎች በብር የተገዙ እና እሱ የፈለገውን እንዲመሰክሩለት ያሰበ ሲሆን ነገሮች እርሱ እንዳሰበው ሊሄዱለት አልቻሉም ፤ ፤ አንድ ሰባኪ ወንጌል በፍርድ ቤት ለምስክርነት ቀርቦ በሀሰት እንደመሰከረና ቀሲስ መስፍን የምስክሮችን ቃል እየሰሙ ውጭ ላለ ሌላ የሀሰት ምስክር ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ለአንድ ቀን መታሰራቸውንና በ2000 ብር ዋስ መለቀቃቸውን ጠቅሰን መጻፋን ይታወቃል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ በምስክርነት በቀረበበት ወቅት ሲመሰክር ከአቃቢ ህግ የቀረበለትን መስቀለኛ ጥያቄ ላይ አንደበቱ ሲያያዝ ተመልክቷል ፤ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ሰምቶ ከጨረሰ በኋላ በ27/09/2004ዓ.ም ተከሳሾች የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያሰሙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር ፤ በጊዜውም የሁሉም ተከሳሽ ምስክሮች ሙዳይ ምጽዋት ተሰበረ በተባለበት እለት ተከሳሾች ከተማ ውስጥ እንዳልነበሩና አንዱ ተከሳሽ በዓል ለማክበት ሳማ ሰንበት እንደነበረ ለፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ፤
በ04/10/2004ዓ.ም በዋለው ችሎት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፖሊስ የምስክሮችን ቃል ለሌላ ምስክር በማስተላለፋቸው አቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርትና ፖሊስ በጊዜው አደረጉ ስለተባለው ተግባር የእምነት ክህደት ቃላቻውን እንዲቀበልና ለቀጣይ ችሎት እንዲያቀርብ ትእዛዝ ተላፏል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ራሱ በጻፈውና የቤተክህነቱን ማህተብ ያለበትን “ቦታው የመድሀኒዓለም አይደለም” የሚል ሀሳብ ያለውን መልዕክት ከሳምንታት በፊት የአካባቢውን ምዕመን ሰብስቦ በአውደ ምህረት ላይ በፖሊስ እየተጠበቀ አንብቦ ነበር ፤ መልዕክቱ ሲጨመቅ “ይህ ቦታ በሽያጭ ለባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት ተስጥቷል ፤ አሁን እኔ የመጣሁት ከጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ ጉዳይ ተወክዬ ነው ፤ ሲኖዶስ የወሰነውን ብጹአን አባቶች የተስማሙበትን ጉዳይ እናንተ መቃወም አትችሉም ፤ ሲኖዶስ የቤተክርስትያኒቱ የበላይ አካል ስለሆነ ውሳኔው መቀበል አለባችሁ ፤ ቤተክርስትያኒቱ ቦታውን መጠየቅ አትችልም ፤ ቦታው የአቶ ታዲዎስ ነው ፤ እናንተ በዚህ ጉዳይ ላይ ብትቃወሙና ፍርድ ቤት ክስ ብታቀርቡ ምንም የምታመጡት ነገር የለም ፤ ቦታውን ለማስረከብ እና ለአፈጻጸሙ ተግባራዊነት ብትተባበሩ ይሻላል ፤” የሚል መልዕክት ነበረው ፤ አቃቢ ህግ “ህዝብን ለአመጽ የሚቀሰቅስ ሁኔታ አቶ ጌታቸው ዶኒ በቤተክርስትያኒቱ አውደ ምህረት ላይ ያነበበው በጽሁፍ እና በቪዲዮ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትለት`` ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ዛሬ ቪዲዮውንና ጽሁፉን ለማየት ቀጠሮ ይዟል ፡፡ ይህም ቪዲዮ እኛ እጅ የሚገኝ ሲሆን የፍርድ ቤቱን የፍርድ ሂደት እንዳያስተጓጉል በመስጋት ብሎጋችን ላይ አላወጣነውም፡፡
ባሳለፍነው እሁድ የባቦጋያ አካባቢ ምዕመናን ከአስተዳዳሪው ጋር በመሰብሰብ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በጊዜው በርካታ ምዕመናን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከቦታው እና ከፍርድ ቤት ጉዳዩ ጋር በማያያዝ አቅርበውላቸዋል ፤ በጊዜው ችግር እንዳይፈጠር በመፍራት ስብሰባው ላይ 30 ፖሊሶች ተገኝተው ነበር ፤ የመጀመሪያው ጥያቄ “ለምን ከአቶ ጌታቸው ዶኒ ጋር በመሆን የመድሀኒዓለምን ታቦት ማረፊያ ቦታ ሬክላም እንዲነቀል አደረጉ ? የተነቀለው መስቀል በእጅዎ ከያዙት መስቀል በምን ይለያል ? ሰውየው ቤተክርስትያኖች ላይ ብዙ ችግር ያደረሰ ሰው ነው ፤ በግሉ የእምነት ተቋም ያቋቋመ ሰው ነው ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ የ2004 ዓ.ም የግንቦት ጉባኤ ላይ ስለ ሰውየው ምንፍቅና የተነጋገሩበት ግለሰብ ነው ፤ ስራው በቪዲዮ ከማስረጃ ጋር የተጋለጠበት ፤ ምዕመኑ ሁሉ ስራውን የሚያውቀው ቤተክርስትያኒቱን ለማፍረስ የተነሳ ግለሰብ ነው ፤ ታዲያ ይህን ሁሉ እያወቁ እንዴት ከዚህ ሰው ጋር በመሆን ከዚህ ሰው ጋር ያብራሉ ? ፤ …… እና መሰል በርካታ ጥያቄዎችን የተጠየቁ ሲሆን … ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲህ በማለት አቅርበዋል “የጠየቃችሁኝ ጥያቄዎች ሁሉ ጠንከር ጠንከር ያሉ ናቸው ፤ እኔም ውስጤ እንደናንተው ጥቂት እምነት አለኝ ፤ እንድመልስ አታስገድዱኝ ፤ ፊልሙን በተመለከተ እኔምአይቸዋለሁ አቶ ጌታቸውን ስጠይቀዉም ፊልሙን ማን እንዳሳተመዉ ንገረኝ ነዉ ያለኝ እንጅ ልክ ነዉስህተት ነዉ አላለኝም ፤ ሰውየው አደረሰ ስለተባለው ነገር የማውቀው ነገር የለም ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መግለጫውንም አላነበብኩም ፤ የሲኖዶስ መግለጫውን አምጡልኝና እኔም ከናንተ ጎን ነው የምቆመው ” ብለዋል፡፡ ይህን እንዳሉ ያልመለሱትን ጥያቄ “ሬክላሙ ለምን እንደተነቀለ አታውቁም ወይስ…. ? በማለት ሌላ ጥያቄ ተከትሏል ፤
ሌላ ምዕመንም “በቦታ ላይ የተተከለው መስቀል በሊቀጳጳሱ ተባርኮ ነው የተተከለው ፤ እርስዎ እጅ ላይ የያዙትን መስቀልም ተባርኮ ነው የተሰጠዎት ፤ መስቀሉ ይነቀል ቢባል እንኳን መነቀል ያለበት በአግባቡ መሆን ሲገባው ከአቶ ጌታቸው ዲኒ ጋር በማበር ይህን ማድረግ አልነበረቦትም” በማለት ገስጸዋቸዋል፡፡ በጊዜው በጥበቃ ላይ የነበሩ ፖሊሶች ከዚህ በፊት በአቶ ጌታቸው አማካኝነት የተነገራቸውና አሁን ደግሞ ቦታው ላይ እየተደረገ ያለው ነገር ተመልክተው ግራ እንደገባቸው ሲወያዩ ተስምተዋል፡፡
በተጨማሪ የመድሀኒዓለም ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት ቀን የቤተክርስትያኒቱ ሰንበት ተማሪዎች እያሉ እንዴት ከሌላ ቦታ ሰንበት ተማሪ ያመጣሉ? ተብለው የተጠየቁ ሲሆን ለዚህም “ማን እንዳመጣቸው እንደማያውቁ” መልስ ሰጥተዋል ፤ በጊዜው የነበሩ ምዕመናን የቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ሆነው ሳለ እንዴት ከየት እንደመጡ አላውቅም ይላሉ? ሲሉ ተሰምተዋል ፤ እነዚህ ሰንበት ተማሪዎች የማምጣቱ ሂደት ላይ የአቶ ጌታቸው ዶኒ እጅ እንዳለበት ለማወቅ ተችሏል ፤ በቤተክርስትያኑ ውስጥ የሚገኙ ሰንበት ተማሪዎች የእነሱን አላማ የሚቃወሙና የቦታን ተላፎ መሰጠት የማይደግፉ በመሆናቸው በዝማሬ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በቀኑ አልተፈቀደላቸውም ፤ በጊዜው የመጡት ሰንበት ተማሪዎች በደብረብርሀን መንገድ በሰንዳፋ በኩል ጨፌ ከሚባል አካባቢ እንደመጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሰባኪ ወንጌል (ቀሲስ ሐይለ እየሱስ) በሀሰት ፍርድ ቤት በመመስከራቸው መጀመሪያ ራስዎ ይማሩ ፤ ከዛ እኛን ለመስበክ ይምጡ ፤ አሁን ግን እኛን መስበክ አይችሉም ፤ አውደ ምህረት ላይም አይቁሙብን ብለዋቸዋል ፤
ይህ የቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ እንደ ቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ጉዳይ የሰው ህይወት እንዳይጠይቅ ብርቱ ጥንቃቄ ቤተክህነቱ እና መንግስት ቢወስዱ መልካም ነው ፤ ጥያቄዎች በጊዜያቸው መልስ አለማግኝታቸው ችግሩን ወደ ባሰ አቅጣጫ ስለሚወስደው ቀድሞ ሊጤን ይገባል ፤ በህዝቡ ላይ ህገወጥ ሆነው ህጋዊ ስራ እንደሚሰሩ የሚያስመስሉትን ለቤተክርስትያን ለህዝብና ለሀገር ሰላም ጠንቅ የሆኑትን እንደ አቶ ጌታቸውን የመሰሉ ሰዎች መንግስት ሀይ ይበላቸው …… በአንድ ሰው ምክንያት ሺዎች መበጥበጥና መታወክ መቻል የለባቸውም፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ምዕመኑ መከራን መሸከም የለበትም ፤ ችግሮች ተጠንተው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል
የቦታውን ጉዳይ በጥልቀት ለማንበብ ይህን ይጫኑ
“እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን”
በርካታ ቤቶችን የበላው የሐዲያ ቃጠሎ እስካሁን መንስዔው አልታወቀም
አንድ አድርገን
(*** Reporter ***):- በደቡብ ክልል ሐዲያ ዞን በታህሳስ ወር በተለያዩ ቀናት 140 ቤቶችን የበላው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ በእስካሁኑ ሒደት አልታወቀም፡፡ በዞኑ ሰሮ፣ ሻሼጌ፣ ጌሌቦ፣ ሚሻና ጊቤ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች በታህሳስ ወር ውስጥ በ15 ተከታታይ ቀናት ድንገተኛ እሳት እየተነሳ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ የቃጠሎው ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ከመሆኑም በላይ፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አካባቢውን እንዲጎበኙ ምክንያት ሆኗል፡፡
Monday, June 11, 2012
ዝቋላን መልሰን እናልማ
“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
ወደ ገዳሙ የሚደረገው የጉዞ ቀን ቅዳሜ ሰኔ 24 2004 ዓ.ም ሲሆን የመመለሻ ቀን ደግሞ እሁድ ሰኔ 25 ይሆናል፤ ይህን የተቀደሰ አላማ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍና ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበልየምትፈልጉ ሰዎች የትራንስፖርት ወጪዎትን ብቻ በመሸፈን ማህበሩ ባዘጋጀው የጉዞ መርሀ ግብር ላይ በመገኝትየታሪካዊውን ገዳም ደን መልሶ የማልማት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ዛፍ የመትከል መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን (ዶማ ወይም አካፋ) መያዝ ይጠበቅቦታል ፤
“የማይቀርበት ታላቅ የበረከት ስራ….”
ይህን አላማ ለመርዳት ወይም መርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ለበለጠ መረጃ (0911-201649 ፤ 0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤ 0924-373474) በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)