Saturday, June 2, 2012

ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ


ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ



(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።


በአሜሪካን አገር “ዋይት ሐውስ ነው የምሠራው” በሚለው ማታለያው ከሲ.አይ.ኤ ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል የዋሆች በማስፈራራት እና “የኢህአዴግ አባል ነኝ” በሚል ብዙዎችን ለማሳቀቅ እና ከእምነታቸውና ከቤተ ክርስቲን አገልግሎታቸው እንዲንራተቱ ለማድረግ በመጣር ላይ የሚገኘው ይኸው ግለሰብ አያሌ ሊቃውንት ባሉባቸው አህጉረ ስብከት የበላያቸው ሆኖ እንደፈቀደው እንዲፏንን እንደተለቀቀ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ እጅግ ሊያስመሰግነው በሚችል መልኩ በተሐድሶ ድርጅቶች እና አራማጆች ላይ የውግዘት ቃሉን ባስተላለፈ ማግሥት ቅዱስነታቸው ቀንደኛውን ተሐድሶ በአሜሪካ የሾሙበት ምክንያት የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ቅስም ለመስበር እንዲሁም ወደ ውጪ አገር ሰው በመላክ ሰበብ የሚያጋብሱትን ገንዘብ በታማኛቸው አማካኝነት ለማካሔድ በማሰብ መሆኑን ምንጮች አብራርተዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ አቡነ ፋኑኤል የቀረቡት አቤቱታዎች በአጀንዳነት እንዳይያዙ፣ በመካከሉም በሚነሡበት ወቅት እልባት እንዳያገኙ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የከረሙት ፓትርያርኩ ይባስ ብለው ኃ/ጊዮርጊስን መላካቸው በሰሜን አሜሪካ የተጀመረውን ተቃውሞ የበለጠ ያጎላው ካልሆነ በስተቀር የሚፈይደው አንዳች ፋይዳ እንደማይኖር ይታወቃል።
ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ
በአሜሪካ ሦስት አህጉረ ስብከት ሲኖሩ የዋሺንግተን ዲሲው በዋና ፀሐፊው  በቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ የኒውዮርኩ በመ/ገነት ቆሞስ አባ ዘርዓ ዳዊት በርኼ፣ የካሊፎርኒያና አካባቢው ደግሞ በሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ ሥራ አስኪያጅነት ሲመራ ቆይቷል።

ር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment