Saturday, August 18, 2012

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል



“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።

የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ቀን ይፋ ሆኗል





(አንድ አድርገን ነሐሴ 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በመንበረ ፓትርያርክ የሀዘን የክብር መዝገብ ተዘጋጅቷል ከ12/12/2004 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያ በብጹ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እረፍት የተሰማውን ስሜት በጽሁፍ ማስፈር ይችላል ተብሏል፡፡ 

የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት እለት ነሐሴ 17/2004 ሀሙስ ከቀኑ 6.00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መሆኑ ተገለፀ:: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቋሚ ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ:: ቅዱስነታቸው 16/12/2004 ረቡዕ ከሰባት ላይ ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስከሬናችው ይሄድና ፍትሃት ሲደረገ አምሽቶ ወደ 11፡00 ላይ በዛኑ ቀን በሰረገላ አስከሬናቸው ሆኖ በብፁዓን አባቶች አጃቢነት ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይገባል ፤ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዚያው ቀን ያድራል ፤ በነጋታውም ከሌሊቱ 11፡00 ጀምሮ በብፁዓን አባቶች መሪነት ቅዳሴ ይደረጋል፤  ከጠዋቱ 300ላይ የቅዱስነታችው አስከሬን ወደ ውጪ በመውጣት የሽኝት ፕሮግራም ይደረጋል  በዚህም ወቅት የተለያዩእንግዶች እንደየደረጃቸው ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል  በመጨረሻም ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖትከተቀበሩበት አጠገብ ሥርዓተ ቀብራቸው ይፍፀማል፡፡

የቅዱስነታቸውን ነፍስ በመንግስተ ሠማያት ያሳርፈው አሜን !!

Thursday, August 16, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ




  • አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ“አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
  • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
  • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል:: (ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
  • “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን”ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
  • በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/READ THIS NEWS IN PDF) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ንጋት ላይ በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

(ሰበር ዜና) ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ዐረፉ

from Daniel kibret's views'

                            ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ 
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር
ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያልታሰበ አደጋ እንዳያመጣ ጥንቃቄ የተሞላ ሃይማኖታዊና ጥበባዊ ሥራ መሥራት አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ አራት ነገሮች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል
  1. የእርሳቸው ደጋፊና ተቃዋሚ በሆኑ አካላት መካከል በሚፈጠር ግጭት ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳትታወክ
  2. ሀብት እና ቅርስን የማሸሽ አዝማሚያ እንዳይከሰት
  3. ቤተ ክርስቲያኒቱን ማን ለጊዜው ይምራት በሚለው ዙርያ በሚፈጠረው ልዩነት አደጋ እንዳይከሰት
  4. በቀጣይስ ማን በወንበሩ መቀመጥ አለበት በሚለው ዙርያ ችግር እንዳይከሰት
አሁን የመረጋጊያ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ለፓትርያርኩ የኀዘን ጊዜ ያውጅ፡፡ ጊዜያዊ ኮሚቴ ያቋቁም፡፡ ነገሮችን በግልጽነት ለሕዝቡ ይፋ ያድርግ፡፡ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ልምድ ይውሰድ፡፡ ማንኛውም የፓትርያርኩ ንብረቶች ወደ ሌሎች ከመጓዛቸው በፊት በጥብቅ ይቀመጡ፡፡ የባንክ ሂሳቦች ይዘጉ፡፡
አሁን የመረጋጊያ ጊዜ ነው፡፡ ለሀገሪቱም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሲባል ቤተ ክርስቲያኒቱን በዚህ ሁኔታ ወደ ጸጥታ ወደብ የሚመራ አመራር ያስፈልጋል፡፡
ዝርዝሩን እንመለስበታለን፡፡


አቡነ ጳውሎስ ………

(አንድ አድርገን ነሐሴ 10 2004ዓ.ም)፡- አቡነ ጳውሎስ በጠና መታመማቸውን ትላንትና ገልጸን ነበር ፤ ዛሬ ደጀ-ሰላም እንደገለጸችው ‹‹Unconfirmed Deje Selam sources say Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is dead. Stay Tuned for the detail.›› በማለት ተዘግቧል ፤ መረጃው ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ የቤተክህነቱን ድምጽ መስማት መልካም ይመስለናል ፤  ለማንኛውም ለሙሉ ዘገባ የቤተክህነቱን ድምጽ ኦፊሺያል በሆነ መልኩ  ሲገለጽ እኛም እሱን እናቀርባለን፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን የተዘገበ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ደጀ ሰላም ዜናውን እየተከታተለች ማቅረቧን ትቀጥላለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

Wednesday, August 15, 2012

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል




. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልመግባታቸው ተሰማ፡፡



አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደ ነበሩ የተናገሩት የዜናው ምንጮች÷ የፓትርያርኩን አጣዳፊ ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡ ይኹንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን ተነግሯል፤ ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አባ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ጤናቸውን ለመከታተል የሚያደርጉት ሳምንታዊ ወጪ ከስድሳ ሺሕ ብር በላይ ማሻቀቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመዋል



(አንድ አድርገን ነሐሴ 9  2004 ዓ.ም)፡- አቡነ ጳውሎስ ከታመሙ ቆየት ብለዋል ነገር ግን ህመሙ የከፋ ባይሆን ፤ ከዓመታት በፊት በደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል በየጊዜው ህክምና እንደሚከታተሉ እናውቃለን ፤ ከእድሜ ጋር አብሮ የሚመጡ በሽታዎችም እንዳሉ ይታወቃል ፤ ባሳለፍነው የሁዳዴ ፆም ጊዜ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ጸሎተ ሀሙስ እለት የቅድሥት ሥላሴን የውስጥ መረማመጃ ደረጃዎች መውጣት አቅቷው ሁለት ሰዎች ከግራና ከቀኝ ደግፈው ደረጃዎቹን ሲያወጧቸው ሲያወርዷቸው ተመልክተናል ፤ ከዚህ በተጨማሪም ከኃላ በምዕመናን ተገፍተው እንዳይወድቁ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከኋላ ደግፈዋቸው ነበር ፤ በጊዜው በአትኩሮት ስንመለከት የነበረው ነገር ራሳቸውን ችለው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ነው ፤ ከዚያ በኋላ ትንሽ ተሸሏቸው ስለነበር አንጻራዊ ለውጥ ይታይባቸው ነበር ፤ አሁን ግን  አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ታመው ወደ ልደታ አካባቢ የሚገኝው ባልቻ ሆስፒታል አምርተዋል፡፡

እግዚአብሔር ይማራቸው የንስሀ እድሜ ይስጣቸው እንላለን

Saturday, August 11, 2012

ቅ/ሲኖዶስ የ”ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮቹን እንቅስቃሴ “ተቀባይነት የሌለው ነው” በሚል እንዲታገድ ወሰነ



  • በመሥራችነት ከተጠቀሱት ግለሰቦች መካከል ስለ እንቅስቃሴው ምንም የማያውቁና በፓትርያርኩ ስም አስገዳጅነት የተሰባሰቡ ይገኙበታል።
  • እንቅስቃሴው ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ብሎጎች ጋራ ያለውን ግንኙነት ይፋ አድርጓል።

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 5/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 11/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት መጽናትና ለአስተዳደራዊ አንድነቷ መጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ውሳኔዎች መጠናቀቁን ተከትሎ÷ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነናዊ አሠራር ለማጠናከርና ቡድናዊ ጥቅሞቹን ለማሳካት ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ፈቃድ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ በመጥራት ኅቡእ እንቀስቃሴ ሲያካሂድ የቆየው ቡድን በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ታገደ፡፡

Virgin Mary 'crosses the finish line' with Olympic gold runner




Meseret Defar of Ethiopia holds up a picture at the London 2012 Olympic Games on August 10, 2012 in London, England. Credit: Alexander Hassens/Getty Images Sport/Getty Images
.- Ethiopian athlete Meseret Defar provided one of the most emotional moments of the London 2012 Summer Olympic Games when she crossed the finish line in the 5000 meter race to win the gold.

She then pulled a picture of the Virgin Mary out from under her jersey, showed it to the cameras and held it up to her face in deep prayer.

An Orthodox Christian, Defar entrusted her race to God with the sign of the cross and reached the finish line in 15:04:24, beating her fellow Ethiopian rival Tirunesh Dibaba, who was the favorite to win.

A teary-eyed Defar proudly showed the picture of the Virgin Mary with the Baby Jesus that she carried with her for the entire race.

Throughout the event, Defar kept pace with three other Ethiopian runners and three from Kenya, until speeding past them on the homestretch to win gold.

The silver medal went to Vivian Cheruiyot of Kenya and the bronze to Dibaba.

Defar is also a two-time world champion in the 3000 meters. In Athens in 2004 she won the gold in the 5000 meters and in Beijing in 2008 she won the bronze.

On June 3, 2006 she broke the world record for the 5000 meters set previously by Turkish runner Elvan Abeylegesse, with a time of 14:24:53.

Wednesday, August 8, 2012

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ AUDIO ያዳምጡ



በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ መሆኑን (ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012) ባወጣነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴንከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ያደረሱትን ዜና አንባብያን ትረዱ ዘንድ ከድምጽ መዝገባችን በጥቂቱ እንድትሰሙት ሁለቱን ክፍል እነሆ እንላለን። እነዚህ ካህናት የሚገኙባቸው አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ የ“ስቀለው-ስቀለው” ጉባኤ የሚሰጡትን መልስም እንጠብቃለን። 
(ክፍል አንድ፤ Part 1) 

ክፍል ሁለት ይዞራል።

በባቦጋያ መድኃኒዓለም የመሬት ጉዳይ የታሰሩት ክርስትያኖች ከእስር ተፈቱ




  • አዲሱ አስተዳዳሪ ሰበካ ወንጌሉንና ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሰብስበው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ሰው   እዚህ ቤተክርስትያን  መጥቶ እንዳያገለግል የሚል መመሪያ ሰጥተዋል

(አንድ አድርገን ነሐሴ 2 2004 ዓ.ም)፡- ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው በባቦጋያ መድኃኒዓለም የጥምቀት ታቦት ማሳደሪያ ቦታ ላይ ከባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት ከአቶ ታዲዎስ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ገልጸን በየጊዜው መረጃ በብሎጋችን ላይ ማውጣታችን ይታወቃል ፤ በአዲሱ የባቦጋያ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን  ፤ በአቶ ጌታቸው ዶኒ እና በሪዞርቱ ባለቤት ጠበቃ አማካኝነት በተሸረበ ክስ ከ13 በላይ ስለ መድኃኒዓለም ቦታ ዘብ የቆሙ ክርስትያኖች  ሰኔ 19 2004 ዓ.ም መታሰራቸው ይታወቃል ፤ እነዚህ ሰዎች ላይ ያለአግባብ በሪዞርቱ ባለቤት እና በጌታቸው ዶኒ የሀሰት ክስና የሀሰት ምስክርነት መሰረት 7 ወር ተፈርዶባቸው መታሰራቸውን  በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ በጊዜውም የተፈረደውን ፍርድ በርካቶች የተቃወሙት ሲሆን ፖሊስ ከፍርድ ቤት የማሰሪያ ትእዛዝ አውጥቶ ሰዎቹን ይዙ በሚሄድበት ጊዜ ከ400 የማያንስ ምእመናን ወደ እስር ቤት በእንባ ሸኝቷቸዋል ፤