Saturday, August 18, 2012

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል



“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።

የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ቀን ይፋ ሆኗል





(አንድ አድርገን ነሐሴ 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በመንበረ ፓትርያርክ የሀዘን የክብር መዝገብ ተዘጋጅቷል ከ12/12/2004 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያ በብጹ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እረፍት የተሰማውን ስሜት በጽሁፍ ማስፈር ይችላል ተብሏል፡፡ 

የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት እለት ነሐሴ 17/2004 ሀሙስ ከቀኑ 6.00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መሆኑ ተገለፀ:: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቋሚ ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ:: ቅዱስነታቸው 16/12/2004 ረቡዕ ከሰባት ላይ ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስከሬናችው ይሄድና ፍትሃት ሲደረገ አምሽቶ ወደ 11፡00 ላይ በዛኑ ቀን በሰረገላ አስከሬናቸው ሆኖ በብፁዓን አባቶች አጃቢነት ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይገባል ፤ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዚያው ቀን ያድራል ፤ በነጋታውም ከሌሊቱ 11፡00 ጀምሮ በብፁዓን አባቶች መሪነት ቅዳሴ ይደረጋል፤  ከጠዋቱ 300ላይ የቅዱስነታችው አስከሬን ወደ ውጪ በመውጣት የሽኝት ፕሮግራም ይደረጋል  በዚህም ወቅት የተለያዩእንግዶች እንደየደረጃቸው ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል  በመጨረሻም ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖትከተቀበሩበት አጠገብ ሥርዓተ ቀብራቸው ይፍፀማል፡፡

የቅዱስነታቸውን ነፍስ በመንግስተ ሠማያት ያሳርፈው አሜን !!

Thursday, August 16, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ




  • አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ“አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
  • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
  • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል:: (ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
  • “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን”ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
  • በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/READ THIS NEWS IN PDF) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ንጋት ላይ በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

(ሰበር ዜና) ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ዐረፉ

from Daniel kibret's views'

                            ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ 
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር
ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያልታሰበ አደጋ እንዳያመጣ ጥንቃቄ የተሞላ ሃይማኖታዊና ጥበባዊ ሥራ መሥራት አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ አራት ነገሮች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል
  1. የእርሳቸው ደጋፊና ተቃዋሚ በሆኑ አካላት መካከል በሚፈጠር ግጭት ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳትታወክ
  2. ሀብት እና ቅርስን የማሸሽ አዝማሚያ እንዳይከሰት
  3. ቤተ ክርስቲያኒቱን ማን ለጊዜው ይምራት በሚለው ዙርያ በሚፈጠረው ልዩነት አደጋ እንዳይከሰት
  4. በቀጣይስ ማን በወንበሩ መቀመጥ አለበት በሚለው ዙርያ ችግር እንዳይከሰት
አሁን የመረጋጊያ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ለፓትርያርኩ የኀዘን ጊዜ ያውጅ፡፡ ጊዜያዊ ኮሚቴ ያቋቁም፡፡ ነገሮችን በግልጽነት ለሕዝቡ ይፋ ያድርግ፡፡ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ልምድ ይውሰድ፡፡ ማንኛውም የፓትርያርኩ ንብረቶች ወደ ሌሎች ከመጓዛቸው በፊት በጥብቅ ይቀመጡ፡፡ የባንክ ሂሳቦች ይዘጉ፡፡
አሁን የመረጋጊያ ጊዜ ነው፡፡ ለሀገሪቱም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሲባል ቤተ ክርስቲያኒቱን በዚህ ሁኔታ ወደ ጸጥታ ወደብ የሚመራ አመራር ያስፈልጋል፡፡
ዝርዝሩን እንመለስበታለን፡፡


አቡነ ጳውሎስ ………

(አንድ አድርገን ነሐሴ 10 2004ዓ.ም)፡- አቡነ ጳውሎስ በጠና መታመማቸውን ትላንትና ገልጸን ነበር ፤ ዛሬ ደጀ-ሰላም እንደገለጸችው ‹‹Unconfirmed Deje Selam sources say Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is dead. Stay Tuned for the detail.›› በማለት ተዘግቧል ፤ መረጃው ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ የቤተክህነቱን ድምጽ መስማት መልካም ይመስለናል ፤  ለማንኛውም ለሙሉ ዘገባ የቤተክህነቱን ድምጽ ኦፊሺያል በሆነ መልኩ  ሲገለጽ እኛም እሱን እናቀርባለን፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን የተዘገበ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ደጀ ሰላም ዜናውን እየተከታተለች ማቅረቧን ትቀጥላለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

Wednesday, August 15, 2012

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል




. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልመግባታቸው ተሰማ፡፡



አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደ ነበሩ የተናገሩት የዜናው ምንጮች÷ የፓትርያርኩን አጣዳፊ ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡ ይኹንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን ተነግሯል፤ ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አባ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ጤናቸውን ለመከታተል የሚያደርጉት ሳምንታዊ ወጪ ከስድሳ ሺሕ ብር በላይ ማሻቀቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመዋል



(አንድ አድርገን ነሐሴ 9  2004 ዓ.ም)፡- አቡነ ጳውሎስ ከታመሙ ቆየት ብለዋል ነገር ግን ህመሙ የከፋ ባይሆን ፤ ከዓመታት በፊት በደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል በየጊዜው ህክምና እንደሚከታተሉ እናውቃለን ፤ ከእድሜ ጋር አብሮ የሚመጡ በሽታዎችም እንዳሉ ይታወቃል ፤ ባሳለፍነው የሁዳዴ ፆም ጊዜ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ጸሎተ ሀሙስ እለት የቅድሥት ሥላሴን የውስጥ መረማመጃ ደረጃዎች መውጣት አቅቷው ሁለት ሰዎች ከግራና ከቀኝ ደግፈው ደረጃዎቹን ሲያወጧቸው ሲያወርዷቸው ተመልክተናል ፤ ከዚህ በተጨማሪም ከኃላ በምዕመናን ተገፍተው እንዳይወድቁ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከኋላ ደግፈዋቸው ነበር ፤ በጊዜው በአትኩሮት ስንመለከት የነበረው ነገር ራሳቸውን ችለው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ነው ፤ ከዚያ በኋላ ትንሽ ተሸሏቸው ስለነበር አንጻራዊ ለውጥ ይታይባቸው ነበር ፤ አሁን ግን  አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ታመው ወደ ልደታ አካባቢ የሚገኝው ባልቻ ሆስፒታል አምርተዋል፡፡

እግዚአብሔር ይማራቸው የንስሀ እድሜ ይስጣቸው እንላለን

Saturday, August 11, 2012

ቅ/ሲኖዶስ የ”ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮቹን እንቅስቃሴ “ተቀባይነት የሌለው ነው” በሚል እንዲታገድ ወሰነ



  • በመሥራችነት ከተጠቀሱት ግለሰቦች መካከል ስለ እንቅስቃሴው ምንም የማያውቁና በፓትርያርኩ ስም አስገዳጅነት የተሰባሰቡ ይገኙበታል።
  • እንቅስቃሴው ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ብሎጎች ጋራ ያለውን ግንኙነት ይፋ አድርጓል።

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 5/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 11/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት መጽናትና ለአስተዳደራዊ አንድነቷ መጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ውሳኔዎች መጠናቀቁን ተከትሎ÷ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነናዊ አሠራር ለማጠናከርና ቡድናዊ ጥቅሞቹን ለማሳካት ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ፈቃድ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ በመጥራት ኅቡእ እንቀስቃሴ ሲያካሂድ የቆየው ቡድን በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ታገደ፡፡

Virgin Mary 'crosses the finish line' with Olympic gold runner




Meseret Defar of Ethiopia holds up a picture at the London 2012 Olympic Games on August 10, 2012 in London, England. Credit: Alexander Hassens/Getty Images Sport/Getty Images
.- Ethiopian athlete Meseret Defar provided one of the most emotional moments of the London 2012 Summer Olympic Games when she crossed the finish line in the 5000 meter race to win the gold.

She then pulled a picture of the Virgin Mary out from under her jersey, showed it to the cameras and held it up to her face in deep prayer.

An Orthodox Christian, Defar entrusted her race to God with the sign of the cross and reached the finish line in 15:04:24, beating her fellow Ethiopian rival Tirunesh Dibaba, who was the favorite to win.

A teary-eyed Defar proudly showed the picture of the Virgin Mary with the Baby Jesus that she carried with her for the entire race.

Throughout the event, Defar kept pace with three other Ethiopian runners and three from Kenya, until speeding past them on the homestretch to win gold.

The silver medal went to Vivian Cheruiyot of Kenya and the bronze to Dibaba.

Defar is also a two-time world champion in the 3000 meters. In Athens in 2004 she won the gold in the 5000 meters and in Beijing in 2008 she won the bronze.

On June 3, 2006 she broke the world record for the 5000 meters set previously by Turkish runner Elvan Abeylegesse, with a time of 14:24:53.

Wednesday, August 8, 2012

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ AUDIO ያዳምጡ



በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ መሆኑን (ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012) ባወጣነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴንከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ያደረሱትን ዜና አንባብያን ትረዱ ዘንድ ከድምጽ መዝገባችን በጥቂቱ እንድትሰሙት ሁለቱን ክፍል እነሆ እንላለን። እነዚህ ካህናት የሚገኙባቸው አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ የ“ስቀለው-ስቀለው” ጉባኤ የሚሰጡትን መልስም እንጠብቃለን። 
(ክፍል አንድ፤ Part 1) 

ክፍል ሁለት ይዞራል።

በባቦጋያ መድኃኒዓለም የመሬት ጉዳይ የታሰሩት ክርስትያኖች ከእስር ተፈቱ




  • አዲሱ አስተዳዳሪ ሰበካ ወንጌሉንና ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሰብስበው የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ሰው   እዚህ ቤተክርስትያን  መጥቶ እንዳያገለግል የሚል መመሪያ ሰጥተዋል

(አንድ አድርገን ነሐሴ 2 2004 ዓ.ም)፡- ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው በባቦጋያ መድኃኒዓለም የጥምቀት ታቦት ማሳደሪያ ቦታ ላይ ከባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት ከአቶ ታዲዎስ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ገልጸን በየጊዜው መረጃ በብሎጋችን ላይ ማውጣታችን ይታወቃል ፤ በአዲሱ የባቦጋያ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን  ፤ በአቶ ጌታቸው ዶኒ እና በሪዞርቱ ባለቤት ጠበቃ አማካኝነት በተሸረበ ክስ ከ13 በላይ ስለ መድኃኒዓለም ቦታ ዘብ የቆሙ ክርስትያኖች  ሰኔ 19 2004 ዓ.ም መታሰራቸው ይታወቃል ፤ እነዚህ ሰዎች ላይ ያለአግባብ በሪዞርቱ ባለቤት እና በጌታቸው ዶኒ የሀሰት ክስና የሀሰት ምስክርነት መሰረት 7 ወር ተፈርዶባቸው መታሰራቸውን  በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ በጊዜውም የተፈረደውን ፍርድ በርካቶች የተቃወሙት ሲሆን ፖሊስ ከፍርድ ቤት የማሰሪያ ትእዛዝ አውጥቶ ሰዎቹን ይዙ በሚሄድበት ጊዜ ከ400 የማያንስ ምእመናን ወደ እስር ቤት በእንባ ሸኝቷቸዋል ፤

Tuesday, August 7, 2012

የአቡነ ጳውሎስ የዶክትሬት ጥናት መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል


በጥናቱ መታተም ስለ ነገረ ማርያም ቅ/ሲኖዶስ በአቡነ ጳውሎስ ላይ ያነሣውን ጥያቄ ለማድበስበስና ወዲያውም ደግሞ የጥቅም አሳዳጆችን ፍላጎት ለማሟላት እንደታለመ ተነግሯል።
ፓትርያርኩ ለእጅጋየሁ በየነ ካባ አልብሰዋል።
ወይዘሮዋ “ለአራት ዓመታት ያረገዝኹት ነው” ያሉትን ‹ፎቶ-መጽሐፍ› አስመርቀዋል፤ ከ‹ፎቶ-መጽሐፉ› ኅትመት ጋራ በተያያዘ እስከ ብር 700,000 ወጪ መደረጉ እየተነገረ ነው።

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 28/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 4/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF):- አምስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡ
ነ ጳውሎስን “ዓለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ ሰውነትና ክብር” ማእከል አድርጎ በተለያዩ ሰበቦች የሚካሄደው የኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው አከባበር አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ይኸው የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለከፍተኛ ብክነትና ዘረፋ እየዳረገ በሚገኘው÷ ከነጻነት በዓል ወደ ግለሰባዊ የተክለ ሰውነት ግንባታ በተቀየረው የበዓል አከባበር ቀጣዩ መድረክ ደግሞ÷ የአቡነ ጳውሎስን የነገረ መለኰት ዶክትሬት ጥናት ጽሑፍ በመጽሐፍ መልክ ማሳተም፣ ማስመረቅና ማሻሻጥ ነው፡፡

የመጽሐፉ ምረቃ ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ በ10፡00 ላይ በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ ፓትርያርኩና በጥንቃቄ የተመረጡ ግለሰቦች በተገኙበት እንደሚከናወን ተጠቁሟል፤ በሰሞኑ የበዓለ ሢመት ድግሶች ከፍተኛ ሚና የነበራቸው እነ እጅጋየሁ በየነና የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ግሩም መልአክ ታዬ ለጥናት መጽሐፉ ኅትመት አስተዋፅኦ ማድረጋቸውም ተነግሯል፡፡

በ1967 ዓ.ም ከሌሎች ሁለት አባቶች ጋራ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ አንብሮተ እድ ኤጲስ ቆጶስነት እንደተሾሙ ለወኅኒ የተዳረጉት አቡነ ጳውሎስ÷ ከሰባት ዓመት እስር በኋላ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አማካይነት ባገኙት የነጻ ትምህርት ዕድል ከአሜሪካው የፕሪንስተን ቴዎሎጂካል ሰሚናሪ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የማስትሬት ዲግሪ ቀጥሎም በነገረ ማርያም ንጽጽራዊ ጥናት ላይ ባተኰረው የነገረ መለኰት ትምህርት ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡

አቡነ ጳውሎስ “Filsata: The Feast of the Assumption of the Virgin Mary and the Mariological Tradition of the Ethiopian Othodox Tewahedo Church” በሚል ርእስ እ.አ.አ በ1988 በነገረ ማርያም ላይ የሠሩት የነገረ መለኰት ዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ከቀድሞው ጀምሮ ውስጥ ለውስጥ ጥያቄ ሲነሣበት ቆይቶ አባ ሰረቀ “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ ባሳተሙት የዶሴ ስብሰብ ሰበብ በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ አቡነ ጳውሎስን ማስጠየቁ ይታወሳል፡፡
“ይመረቃል” በተባለው መጽሐፍ በተለይም የእመቤታችንን ንጽሕና አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያናችንን በማይወክል መልኩ በአቡነ ጳውሎስ ንጽጽራዊ ጥናት ውስጥ የእኛ መስሎ የተገለጸው የባዕዳን ትምህርት እርምት ተደርጎበት እንደኾን ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ግንቦት ዘጠኝ ቀን 2004 ዓ.ም በመጽሐፉ ላይ ስላካሄደው ስብሰባ “የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰባተኛ ቀን ውሎ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአቡነ ጳውሎስ ኮመጠጠ” በሚል ርእስ ያቀረብነውን ዘገባ ከፊል ይዘት የሚከተለው ነበር፡፡

. አቡነ ጳውሎስ በእመቤታችን ንጽሕና ላይ እምነታቸውን እንዲገልጡ ቢጠየቁ አንደበታቸው ተሳሰረ፤ ለጥያቄው መነሻ የኾነው ፓትርያርኩ በአባ ሰረቀ ‹መጽሐፍ› ላይ ስለተጠቀሰው የዶክትሬት ጽሑፋቸው ዝምታን በመምረጣቸውና ኮሚቴውም የእርሳቸውን ምላሽ ወይም አቋም አለመመርመሩ ነው - “አባ ሰረቀ ጽሑፍዎን ጠቅሰው መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ ለምን ዝም አሏቸው? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም? ይሉኝታ ነው ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው?” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም - ነደ ‹ተሐድሶ›/
ይኹንና ኮሚቴው በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ በየደረጃው ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ የተናነቃቸው ርእሰ መንበሩ አቡነ ጳውሎስ ያንን በመገልበጥ ሌላ የውሳኔ ሐሳብ ይዘው በመቅረብ ያነባሉ፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም አቡነ ጳውሎስ ያነበቡት ትላንት ካዳመጡት የሚለይባቸውን ነጥቦች በመጥቀስ ቀደም ሲል በቀረበው ወደ ውሳኔ መሄዱ የተሻለ መኾኑን ይናገራሉ፡፡ አቡነ ጳውሎስ ግን የኮሚቴውን አባላት ሌሎች ተናጋሪዎችን “እናንተ ባቀረባችኹት አላምንበትም፤ ኮሚቴው በትክክል እና በጥራት አልሠራም፤ ሪፖርቱ ችግር አለበት፤ አልቀበለውም” በማለት ፍርጥም ይላሉ፡፡

ይህን ጊዜ ነበር ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተነሥተው “አዎ፣ ችግር አለ፤” አሉ “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ አባ ሰረቀ ያሳተሙትን መጽሐፍ መሰል ጥራዝ በማስታወስ ንግግራቸውን ሲጀምሩ፤ “አዎ ችግር አለ፤ ዝምድና ነው፣ ይሉኝታ ነው፣ ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው ኮሚቴው እርስዎን ያልጠየቀው? አባ ሰረቀ ከእርሰዎ ጽሑፍ በመጥቀስ እመቤታችን ጥንተ አለባት እንደሚሉ አውጥተዋል፤ እውነት ይህ ቃልዎ ነው? እንዲህ ብለዋል? መጽሐፉ ከወጣስ በኋላ ለምን በዝምታ አለፉት? ትክክል ነው ብዬአለኹ፤ ካላሉ ደግሞ አላልኹም ብለው ለምን አልተናገሩም? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም?” የሚል ጠንካራ ጥያቄ አንሥተዋል፡፡

የብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥያቄ ሰበቡ የአባ ሰረቀ “እውነትና ንጋት” ይኹን እንጂ አቡነ ጳውሎስ በፕሪንስተን ቴዎሎጂ ኮሌጅ “Filsata: The Feast of the Assumption of the Virgin Mary and the Mariological Tradition of the Ethiopian Othodox Tewahedo Church” በሚል ርእስ እ.አ.አ በ1988 በነገረ ማርያም ላይ የሠሩት የነገረ መለኰት ዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ከቀድሞው ጀምሮ ውስጥ ለውስጥ ሲነሣ የቆየ ነው፡፡

በነገረ ማርያም ላይ የኢኩሜኒዝም አንድነት(Ecumenical Unity) ለማምጣት በሚል ዓላማ የተሠራው ይኸው ጥናት በአቀራረቡ ንጽጽራዊ ሲኾን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን (ከገጽ 45 - 306)፣ የሮም ካቶሊክን (ከገጽ 307 - 320)፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስን (ከገጽ 333 - 348) እና የፕሮቴስታንት አብያተ እምነትን (ከገጽ 321 - 332) የነገረ ማርያም አስተምህሮ እየራሱና በንጽጽር የቀረበበት ነው፡፡ ለዚህም በታሪክ የተደረገ የንግግር ጥረቶችን በማስታወስ በቀጣም በክርስትናው ዓለም አንድ የተዋሐደ የነገረ ክርስቶስ አስተምህሮ መደረስ እንደሚቻል ይመክራል፡፡

አባ ሰረቀ በመጽሐፍ መሰል የዶሴ ጥራዛቸው የጠቀሱት ከገጽ 336 - 338 ያለውን የጥናቱን ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል ግን አቡነ ጳውሎስ በተለይም የምሥራቅ ኦርቶዶክስን (መለካውያን) የነገረ ማርያም አስተምህሮ ታሪክና ምንነት የዘረዘሩበት ነው፡፡ አባ ሰረቀ እንደ እነአስተርኣየ ጽጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ነገረ ማርያም ከሌሎች ጋራ ለመቀየጥ ካልፈለጉ በቀር አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ባቀረቡበት ክፍል ከአንድ በላይ አስረጅዎችን ለመጥቀስ በቻሉ ነበር፡፡

በዚህ ክፍል (በተለይ ከገጽ 45 - 141) ፓትርያርኩ ነገረ ማርያምን በቅዱስ ያሬድ፣ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ድርሳናት ውስጥ ደኅና አድርገው የተነተኑትን ያህል በአንዳንድ መሠረታዊ ጉዳዮች ግን “የአስተምህሮ አንድነት አመጣበታለኹ” ለሚለው አካዳሚያዊ ፕሮጀክታቸው ይመስላል ከኢትዮጵያ ምንጮች የማያገኙትን አስተምህሮ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይትበሃል ካልታቃኑት ምንጮች ሲጠቅሱ እናገኛቸዋለን፡፡

ለአብነት ያህል በዚሁ ክፍል አቡነ ጳውሎስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነፍስዋም በሥጋዋም ንጽሕት (በሁለት ወገን ድንግል) የኾነችና በክርስቶስ የማዳን ሥራ ያልተለየች ብትኾንም ከውርስ ኀጢአት ግን ነጻ እንዳልነበረች የጻፉት የቅብጦችን ምንጭ ጠቅሰው ነው፡፡ አቡነ ጳውሎስ ምንጩን ጠቕሰው በጥናታቸው እንዲህ ይላሉ፡-

For the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church the Virgin Mary is the example par excellence of obedience and faithfulness to God. She is two-fold virgin; i.e, virgin both in body and soul, who, though not “immaculate” or free from original sin, yet was all-holy, pure, chose to actively participate in the saving work of God, His Incarnation. (p.306) (Amba Alexander, “The Assumption in the Liturgy of the Church of Alexanderia;” Eastern Churches Quarterly, 9 (1951)

በአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና (በ1986 ዓ.ም) በቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፈቃድ በተሰበሰቡ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና 11 ሊቃውንት “ወኢረኵሰት በኢምንትኒ እምዘፈጠራ፤ ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ርኵስ ነገር አልተገኘባትም፤ በነፍስም በሥጋም ሁልጊዜም ንጽሕት ናት፤” (ሃይ. አበ 53) በማለት በቅዱሳን አበው የተመዘገበውን መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዐተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት” መጽሐፍ ግን ስለ እመቤታችን ክብር፣ ንጽሕናና ቅድስና የሚለው የሚከተለውን ነው፡-

“ቤተ ክርስቲያናችን የምታምነውና የምታስተምረው፡- አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት፣ መርገመ ሥጋ፣ መርገመ ነፍስ የሌለባት፣ ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች፣ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ ሐሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች፣ ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት፡፡”

አቡነ ጳውሎስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞተች ስለ ተባለ “የበደል ውርስ አለባት” ብለው ከሚያምኑ ጸሐፊዎች ጋራም ተባብረዋል፡፡ እነ ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌም የሚሉት እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህም ከአበው ድርሳናት ምስክርነት ቢያጡ የጠቀሱት ከቅብጦቹ ምንጭ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፡-

Like all daughters and sons of Adam, the holy Virgin Mary died as a result of Adam’s sin. “Mary sprung from Adam, died on consequence of original sin; Adam died in consequence of sin, and the flesh of the Lord, sprung from Mary, died to destroy sin.” (p.302) (Malaty, T.Y. St. Mary in the Orthodox Concept, 1978)

ይህን ሐሳብ በተመለከተ አባ ሰረቀን ጨምሮ እነ ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌና ሌሎችም “ስሜን (ሥራዎቼን) በመጥቀስ ማታለያ አድርገውኛል” ያሉት ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ግለሰቦቹ እሳቸውን በእነርሱ የኑፋቄ ሐሳብ ውስጥ እንዳይጨምሯቸው፣ ለራሳቸው እንዲመለሱና እንዲታገሡ በመከሩበት “ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ” በሚል ርእስ ባዘጋጁት የመጨረሻ መጽሐፋቸው፡- “እነ ቄስ አስተርኣየ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞተች ስለተባለ የበደል ውርስ እንዳለባት አድርገው ሊቈጥሩት ሞክረዋል፡፡ ክሕደቱ፣ በደሉ ካልቀረ ሰው የኾነ አምላክ ልጇም የመስቀልን ሞት ተቀብሏልና ከአይሁድ ጋራ ቆመው የጲላጦስን ምስክርነት ቢያስተባብሉ ይሻላል፡፡ ከአበዱ ወዲያ በመንገዱ መሄድ መስነፍ ነው ይባል የለ?” በማለት ተችተዋል፡፡

እንግዲህ ትናንት አቡነ ጳውሎስ በእመቤታችን ክብር፣ ንጽሕናና ቅድስና ላይ “እምነትዎን ይግለጡ፤ ይመኑ ወይም ያስተባብሉ” ሲባሉ ወዲያና ወዲህ በሚላጉ ንግግሮች አንደበታቸው መተሳሰሩ ነው የተዘገበው፡፡ ከዚህ በኋላ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት 60 ገጽ ያለው የኮሚቴው ሰነድ በቁጥራቸው ልክ ተባዝቶ እንዲደርሳቸውና እያንዳንዱን የውሳኔ ሐሳብ በጥንቃቄ እየተመለከቱ ለመወሰን ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ነገ ግንቦት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የሚከበረውን የማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ “ወደ አኵስም እሄዳለኹ” የሚለው የፓትርያርኩ ሐሳብ ያሰጋቸው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በይደር የተያዘው አጀንዳ በውሳኔ ሳይታሰር እንዳይቀር የሚያስጠነቅቅ ማሳሰቢያ ተናግረዋል - “በሐዋርያት ቃል፣ በሐዋርያት ቃል÷ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ይህ አጀንዳ ሳምንትም ቢፈጅብን እርስ በርሳችን ሳንፈታተሽ አንድ ሰው እንዳይሄድ!”

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

Sunday, July 1, 2012

ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል



·        አራት መነኰሳት በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል፤ ሌሎቹ መነኰሳት እየተደበደቡ ተበታትነዋል።
·        የገዳሙ የሱባኤ ወቅት በፖሊስ የኀይል ርምጃ እየታወከ ነው።
·        በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግድብ የሚሠራው ሱር ኮንስትራክሽን  ለቆ መውጣቱ እየተነገረ ነው፤ በምትኩ የቻይና ተቋራጭ የገባ ቢኾንም በእርሱም ላይ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰምቷል።
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 24/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 1/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከማይ ፀብሪና ዓዲ አርቃይ ወረዳዎች በአምስት መኪና ተጭነው በመጡ የፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ሥምሪት ውስጥ እንደሚገኝ የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡

አጀንዳችን አንድ ነው - ሃይማኖታችን እና ቤተ ክርስቲያናችን ብቻ!!!!!!


To Read, Print & share, click HERE (PDF).
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 13/ 2011)፦  ላለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናሳስብ እንደቆየነው ቤተ ክርስቲያናችንን ከፊት ከኋላ፣ ከግራ ከቀኝ እና ከውስጥ ጠፍንገው የያዟት ችግሮች የበለጠ እየተገለጡ፣ ፈተና የሆኑባት ግለሰቦችም የበለጠ እየታወቁ፣ በሕዝቡ ዘንድ ይፈጥሩ የነበሩትም ብዥታና ግርታ የበለጠ እየጠራ በመምጣት ላይ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጪም ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት ቢሆንም ከውስጥ ተቀምጠው፣ እንጀራዋን እየበሉ ተረካዛቸውን የሚያነሱባት ግን ፋታ የሚሰጧት አልሆኑም። እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና የተሰጣቸውን አደራ አራካሾች ሳናሰልስ ተግባራቸውን በመቃወምና ለምእመኑም ለማሳወቅ በመጣር ላይ እንገኛለን። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች የተንጠለጠሉበት ካስማ ደግሞ ሁለት ነው። አንደኛው ሙስና፣ ሁለተኛው ኑፋቄ። ደጀ ሰላምም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሰፈነውን ሙስና ትቃወማለች፣ ሰርገው የገቡትን መናፍቃን እና የሚዘሩትን ኑፋቄ ትጸየፋለች። ምን ማለታችን እንደሆነ እናብራራው።

Monday, June 25, 2012

የእመቤታችን ተዓምር


(አንድ አድርገን ሰኔ 18 2004 ዓ.ም)፡- ቀኑ እለተ ሰንበት ሰኔ 17 2004 ዓ.ም  ፤ ሰንበት እንደመሆኑ የት ሄጄ እንደማስቀድስ ሳወጣ ሳወርድ ውስጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያር ገዳም ቤተክርስትያን እንድሄድ አመላከተኝ ፤ ቦታው ጦር ኃይሎች ወደ ወይራ-ቤተል ሲሄዱ አጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ የምትገኝ ቤተክርስትያን ናት ፤ በጣም በጠዋት በመነሳት ካህናት ቅዳሴ ሳይገቡ ለመድረስ ተጣደፍኩኝ ፤ እንደ ሃሳቤም ተሳቶልኝ ቅዳሴ ሳይገቡ መድስረስ ቻልኩኝ ፤ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ደስ በሚያሰኝ እኛ ውስጥን ሀሴት በሚሞላ መልኩ ቅዳሴው ተጠናቀቀ ፡፡ ከዚያ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ የቀኑ ተዓምረ ማርያም ተነበበ ፤ ምዕመኑ ሁሉ ቆሞ ፍጹም በሆነ ፀጥታ የእመቤታችንን ተዓምር አደመጠ፡፡